Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አድዋ ድል መታሰቢያ
  • Address ፒያሳ አራዳ ህንጻ ፊት ለፊት አድዋ ድል መታሰቢያ አስተዳደር ቢሮ ፋይናንስ ክፍል : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251-987929292
  • Website
  • Deadline10 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price600.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያው የገንዘብ መጠን በየ ሎቱ የተለያየ ነው።
  • opening date2025-12-10 00:00:00
  • Categories Building Materials , Office Supplies And Services , Printing And Publishing , Stationery Materials , Electrical Materials , Camera

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአድዋ ድል መታሰቢያ በጨረታ መለያ ቁጥር፡- አ/ድ/መ/-003/2018 /2018 በጀት አመት የሚያስፈልጉትን የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎች የሆኑ ስቴሽነሪና የህትመት ስራዎች ፤ ካሜራና እክሰሰሪ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የሳኒቴሽን እና የግንባታ እቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አድዋ ድል መታሰቢያ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአድዋ ድል መታሰቢያ በጨረታ መለያ ቁጥር፡- አ/ድ/መ/-003/2018 /2018 በጀት አመት የሚያስፈልጉትን የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎች የሆኑ ስቴሽነሪና የህትመት ስራዎች ፤ ካሜራና እክሰሰሪ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የሳኒቴሽን እና የግንባታ እቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆናችሁ ተጫራቾች እንድትሳተፉ እየጋበዝን የእቃዎቹ ዝርዝር ከታች ባለው ሰንጠረዥ ተመላክቷል።

 

ምድብ ቁጥር

የሚገዙ እቃዎች አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ ብር

ሎት 1

የስቴሽነሪ እና የህትመት እቃዎች ግዥ

5000 ብር

ሎት 2

ካሜራና የካሜራ አክሰሰሪ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች

10,000 ብር

ሎት 3

የሳኒቴሽን እና የግንባታ እቃዎች

5,000 ብር

 

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 600/ ስድስት መቶ ብር/ በአድዋ ድል መታሰቢያ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው አካውንት ቁጥር 1000613546867 በመክፈል ደረሰኝ ስሊፕ/ ይዞ በመቅረብ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ይህ ጨረታ በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ይሆናል።
  5. የጨረታው ሰነድ መመለሻ የመጨረሻ ቀን 01/04/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ነው።
  6. ጨረታው በቀን 01/04/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት ማለትም በቀን 01/04/2018 ዓ.ም በ4፡30 ሎት-1 ይከፈታል። ሎት-2 በ02/04/2018 3፡00 ሰዓት ይከፈታል። ሎት 3 በ03/04/18 በ3:00 ሰዓት ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች ሌሎች መረጃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
  8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
  9. የጨረታ ሰነዱ ፒያሳ አራዳ ህንጻ ፊት ለፊት የአድዋ ድል መታሰቢያ እስተዳደር ቢሮ ሊቭል -2 ፋይናንስ ክፍል ይገኛል።

አድራሻ፡- ፒያሳ አራዳ ህንጻ ፊት ለፊት አድዋ ድል መታሰቢያ አስተዳደር ቢሮ ፋይናንስ ክፍል

ስልክ ቁጥር:- +251-0990451200

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአድዋ ድል መታሰቢያ

 

Save Tender