Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Athletics federation (የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን)
  • Address ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንጻ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116-47-97-94
  • Websitehttps://eaf.org.et/
  • Deadline09 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
  • opening date2025-12-09 00:00:00
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ አላቂ የሆኑ የስቴሽነሪ እና የጽዳት ዕቃዎች ግዥ በሀገር ውስፕ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Ethiopian Athletics federation (የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን)


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ አላቂ የሆኑ የስቴሽነሪ እና የጽዳት ዕቃዎች ግዥ በሀገር ውስፕ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡-

  1. በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ጨረታውን በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማደመስስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ጉርድ ሾላ በሚገኘው በፌዴሬሽኑ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መገዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሱፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በፌዴሬሽኑ ቢር ቁጥር 5 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን በ4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት 4:30 ሰዓት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 (መሰብሰቢያ አዳራሽ) ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሣጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ዕቃ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሰነሩባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ተጫራቾች የሚጫረቱት በዘርፉ የተሰማሩ መሆን አለባቸው።

 

አድራሻ:- ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6

ለበለጠ መረጃ:- 0116-47-97-94/ 0116-47-95-78 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ፋክስ፡- 0116-45-08-79 ፖ.ሳ.ቁ 13336

 

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

 

Save Tender