Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለሰሜን ሸዋ ዞን እንፆኪያ ወረዳ ፍርድ ቤት አገልግሎት የሚውሉ -ሎት 1- የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2- ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 3- ሕትመቶች፣ ሎት4 - የፅዳት ዕቃዎች ሎት5 -የህንፃ መሳሪያ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን አንፃኪያ ወረዳ ፍርድ ቤት


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለሰሜን ሸዋ ዞን እንፆኪያ ወረዳ ፍርድ ቤት አገልግሎት የሚውሉ -ሎት 1- የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2- ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 3- ሕትመቶች፣ ሎት4 - የፅዳት ዕቃዎች ሎት5 -የህንፃ መሳሪያ ዕቃዎች

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፤

1.     ተጫራቾች ህጋዊ እና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ እና ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2.     በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 150 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ በመክፈል ከቀን 14/03/2018 ዓ.ም እስከ 28/3/2018 ዓ.ም ከቀኑ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰአት በአንፆኪያ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡

3.     የጨረታ ሰነዱ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ላይ እና ዋጋው መሙያው ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በግልፅ በማስቀመጥ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይቻላል፡፡

4.     የጨረታ ሳጥኑ በቀን 29/3/2018 ቀን 4፡01 ሰአት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን 29/3/2018 ዓ.ም በቀን 4፡30 ሰአት ይከፈታል፡፡

5.     ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ እንደተጫራቾቹ ምርጫ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በጥሬ ገንዘብ /CPO/ ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል።

6.     የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለተሸናፊዎች አሸናፊ ውል ከፈፀመ በኋላ የሚመለስ ሲሆን ለአሸናፈው ድርጅት ውል ፈፅሞ 10% የውል ማስከበሪ እንዳስያዘ የጨረታ ማስከበሪያው ይመለስለታል፡፡

7.     አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀበት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀኖች ውስጥ ውል መግባት ይጠበቅበታል፡፡ ያስያዘው 10% የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን እቃ ሙሉ በሙሉ በአንፆኪያ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መጋዘን ካስረከበ ከ30 ቀናት በኋላ ይመለስለታል፡፡

8.     በሎት 2 የምትወዳደሩ ተጫራቶች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባችሁ፡፡

9.     ፍርድ ቤቱ የሚገዛውን ዕቃ ብዛት 20% የመጨመር እና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡

11. ተጨማሪ መረጃዎችንና የጨረታ ሰነድ በአንፆኪያ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር12 ማግኘት ይችላሉ፡፡

12. ውድድሩ የሚደረገው በእያንድንዱ ሎት በጥቅል ድምር ዋጋ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 033-444-0341/0030 ይደውሉ

ማሳሰቢያ፡- የሚከፈትበት ቀን በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

 

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን አንፃኪያ ወረዳ ፍርድ ቤት

Save Tender