Tender Detail

Tender Details


በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜ ውርስ የተደረጉ የተለያዩ የልጆች ጌጣጌጥ እና የልደት ማከበሪያ እቃዎች፣ የሕክምና እቃዎች፣ ቁርጥራጭ መዳብ እና አልባሳት በግልፅ እንዲሁም charg pin፣ ባጃጅ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የቴሌቪዥን ተገጣጣሚ እቃዎች፣ ጃንጥላ፣ Layer 3 Enthernet swich፣ ጫማ እና ኮስሞቲክስ በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር - 13/2018 ዓ.ም

 

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜ ውርስ የተደረጉ የተለያዩ የልጆች ጌጣጌጥ እና የልደት ማከበሪያ እቃዎች፣ የሕክምና እቃዎች፣ ቁርጥራጭ መዳብ እና አልባሳት በግልፅ እንዲሁም charg pin፣ ባጃጅ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የቴሌቪዥን ተገጣጣሚ እቃዎች፣ ጃንጥላ፣ Layer 3 Enthernet swich፣ ጫማ እና ኮስሞቲክስ በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተጫራቾች መመሪያ የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን መስፈርቶቹ፡-

  1. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ሲሆን ተሽከርካሪ መጫረት ለምትፈልጉ ንግድ ፈቃድ የማይጠይቅ በመሆኑ ማንኛውም እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ግለሰብ መጫረት ይችላል።
  2. የዚህ አንቀፅ ተራ ቁጥር (1) ድንጋጌ ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 2 ሚሊዮን በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ሰርተፍኬት) ማቅረብ አያስፈልገውም፡፡
  3. በተጠቀሰው መስፈርት በጨረታ የሚሸጠው እቃ በኮሚሽኑ ቁጥጥር ስር ከመግባቱ በፊት ባለቤት የነበረ ወይም የባለቤቱ ወኪል ወይም ቤተሰብ የሆነ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡
  4. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ አይነትና ብዛት የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) እየከፈሉ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 6ኛው ቀን 3፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታው የዕቃዎችን ዝርዝር በያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝና በፊደል ገልፀው እና በተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለፁትን በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 3፡50 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።
  6. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ስድስተኛው ቀን በጉምሩከ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን፤ ግልፅ ጨረታው 3፡50 ሰዓት ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ሐራጅ ጨረታው 4፡30 ሰዓት የሚጀመር ይሆናል።
  7. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በመክፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ከፍለው የማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ እቃው እንደገና ለጨረታ ይቀርባል፡፡
  8. ተጫራቾች ለእቃዎች በሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ አሸናፊ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ 15% (VAT) የሚጨመርበት ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን ድረስ ለሽያጭ የተዘጋጁ እቃዎችን በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ እና ስድስተኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ እቃዎች የሰጡትን የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና ለሐራጅ ጨረታ የእቃው መነሻ ዋጋ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ለሆነ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 /ሁላት መቶ ሺህ ብር/ እንዲሁም የእቃው መነሻ ዋጋ ከ2 ሚሊዮን ብር በታች ለሆነ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 033 551 06 93  ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

 

Save Tender