በቂርቆስ ክ/ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ላይ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ዕቃ /አገልግሎት ይፈልጋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቂርቆስ ክፍል ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ፤ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ግዥ ቡድን
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር 02/2018 ዓ.ም
በቂርቆስ ክ/ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ላይ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ዕቃ /አገልግሎት ይፈልጋል።
ሎት የጨረታ ማስከበሪያ በሲኦፕ
ሎት 1. የሰራተኞች ካፍቴሪያ አገልግሎት 20,000
ሎት 2. የህክምና ዕቃዎች 20,000
ሎት 3. የጽህፈት መሳሪያዎች 5,000
ሎት 4. የህዝብ ማመላለሻ መኪና ኪራይ 5,000
ሎት 5. የጭነት መኪና ኪራይ 5,000
ሎት 6. የህትመት ውጤቶች 10,000
ሎት 7. የመድረክ ማስዋብና ቅስቀሳ ስራዎች 5,000
ሎት 8 የድንኳንና ወንበሮች ኪራይ 5,000
ሎት.9 ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 20,000
ሎት.10 ጫኝና አውራጅ/የጉልበት 5,000
ሎት.11. የጄኔሬተር ጥገናና ሰርቪስ አገልግሎት 5,000
ሎት 12 የኤሌክትሪክ መለዋወጫ ዕቃዎች 5,000
ሎት 13 ለቢሮ ልዩ ልዩ አገልግሎት 2,000
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታ እንዲሳተፉ እንጋብዛለን ።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት በአቅራቢነት የተመዘገቡ የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር /TIN NO/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ያላቸው።
- የጨረታ ሰነድ አቀራረብ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናል፣ ቴክኒካል ሰነድ ኮፒ፣ ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናል፣ፋይናንሻል ሰነድ ኮፒ ለየብቻው እንዲሁም ሲፒኦ /CPO/ በባንክ የተረጋገጠ ለብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው። በተጨማሪ የስፔስፍኬሽን ሰነድ ለብቻ በካኪ ፖስታ አሽጓ ማስገባት ግዴታ ነው።
- በጨረታው ላይ ጥቃቅንና አነስተኛ ይበረታታሉ ሆኖም ግን የጨረታ ሰነዱን በነጻ ለማግኘት የሚችሉት ከተቋማት የበላይ ሀላፊዎች ተገቢና የተሞላ ማስረጃ ሲያቀርቡ ብቻ ነው።
- ናሙና የሚያስፈልጋቸው ማቴሪያሎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙበት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቫትን ጨምሮ ማስገባት ይኖርበታል።
- የጨረታ ሰነዱን እስጥፋኖስ ቤ/ክርስቲን አካባቢ በሚገኘው የቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር ህንጻ 6 ኛ ፎቅ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የፋይናንስና አስተዳደር የግዥ ቡድን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጠበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የሚከፈተው ደግሞ በ 11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫረቾች በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ጨረታው ይከፈታል።
- አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ከ7 ተከታታይ የስራ ቀናት በኃላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪ በማስያዣ 8 የስራ ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለበት።
- የካፍተሪያ ጨረታ ላይ የሚሳተፉ አካላት የምግብና መድሃኒት የተረጋገጠ ክሊራንስና የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ አለበት።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የሰነድ መግዣ 400 ብር በድርጅቱ አካውንት ቁጥር 1000001455293 ቂርቆስ ክ/ከተማ አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ቢል ገቢ እንድታደርጉና የገቢ ደረሰኙን ብቻ ይዛችሁ በማቅረብ አገልግሎቱን እንድታገኙ እናሳውቃለን።
አድራሻ
እስጢፋኖስ ከሚገኘው ከማሪዎት ሆቴል ፊት ለፊት የቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር 6 ኛ ፎቅ
ስልክ፡- 011 558 2871
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቂርቆስ ክፍል ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ፤ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ግዥ ቡድን
