Tender Detail

Tender Details


የደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል የጽ/መሳሪያ፣የዕዳት እቃ፣የደንብ ልብስ ግዥ፣የተለያዩ ህትመቶች፣የመብራት ዕቃ፣ዉሃ እቃዎች፣የቢሮ መገልገያ እቃዎች (ፈርኒቸሮች ፣ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣የመኪና ጎማ፣ መለዋወጪያ ፣ዘይት እና የወንበር ልብስ እንዲሁም የአከስጅን ሙሌት ከነማጓጓዣ እና ጫኝና አውራጅን ጨምሮ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል የጽ/መሳሪያ፣የዕዳት እቃ፣የደንብ ልብስ ግዥ፣የተለያዩ ህትመቶች፣የመብራት ዕቃ፣ዉሃ እቃዎች፣የቢሮ መገልገያ እቃዎች (ፈርኒቸሮች ፣ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣የመኪና ጎማ፣ መለዋወጪያ ፣ዘይት እና የወንበር ልብስ እንዲሁም የአከስጅን ሙሌት ከነማጓጓዣ እና ጫኝና አውራጅን ጨምሮ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት:-

  • በዘመኑ) የበጀት ዓመት የታደሰ ወይም አዲስ የወጣ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፈቃድ ያላቸዉ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ ፡፡
  • የግዥ መጠኑ 200,00.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሆስፒታሉ የእለት ገንዘብ ቤት መግዛት ይችላሉ ፡፡
  • ተጫራጮች ለሚወዳደሩበት ሎት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ከዚህ በታች በተመለከተው ሰንጠረዥ መሰረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆስፒታሉ ገንዘብ ቤት ገቢ በማድረግ የተከፈለበትን ደረሰኝ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አብረው አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

ተ.ቁ

ሎት

የግዥው አይነት

የጨረታ ሰነድ መሸጫ ብር

የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን

ምርመራ

1

ሎት1

የጽ/መሳሪያ

200

20,000

 

2

ሎት2

የፅዳት እቃ

200

10,000

 

3

ሎት3

የደንብ ልብስ ግዠ

200

10,000

 

4

ሎት4

የተለያዩ ህትመቶች

200

25,000

 

5

ሎት5

የመብራት ዕቃ

200

10,000

 

6

ሎት6

ዉሃ እቃዎች

200

20,000

 

7

ሎት7

የቢሮ መገልገያ እቃዎች /ፈርኒቸሮች/

200

10,000

 

8

ሎት8

ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች

200

25,000

 

9

ሎት9

የመኪና ጎማ ከነከለመደዳሪው ፣ዘይትና መለዋወጪያ እቃ እንዲሁም የወንበር ልብስ

200

20,000

 

10

ሎት10

የኦክስጅን ሙሌት ከነማጓጓዣ እና ጫኝና አውራጅን ጨምሮ

200

15,000

 

ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦሪጅናሉንና ኮፒ በጥንቃቄ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፣

  • ሁሉም ተጫራቾች በእያንዳንዱ የሥራ ዝርዝርና የተጫራቾች መመሪያ መሰረት የመፈፀም ግዴታ አለባቸዉ፡፡
  • ተጫራቾች ለሚሳተፉበት ጨረታ ህጋዊና ተቀባይነት እና አግባብነት ያለዉ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸዉን ጨረታውች በሆስፒታሉ የጨረታ ሰነድ አይነትና ዝርዝር /ስፔስፊኬሽን / መሰረት ማቅረብ አለባቸዉ ፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን እቃ የተመረተበትን ሀገርና ብራንድ መጥቀስ አለባቸዉ ፡፡
  • ተጫራቾች የሚያቀርቡትንና ዋጋ የሞሉበትን እቃ አይነት እያንዳንዱ ናሙና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው ናሙና አያይዘው ካላቀረቡ እና በዋጋ አሸናፊ ከተደረጉ ሆስፒታሉ በሚመርጠው ናሙና መሰረት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ ጥራት ያለዉና አንደኛ ደረጃ ሆኖ በገበያ ላይ ተመራጭነት ያለዉ መሆን አለበት፡፡
  • ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ ከማቅረባቸዉ በፊት ናሙና በማቅረብ ትከከለኛነቱ ከተረጋገጠ በኋላ በራሳቸዉ ወጭ በማቅረብ ለሆስፒታሉ ንብረት ከፍል ማስረከብ አለባቸዉ፡፡ሆስፒታሉ የእቃዉን ጥራትና በናሙናዉ መሰረት የቀረበ መሆኑን በሚመለከታቸዉ ባለሞያዎችና ሃላፊዎች በማረጋገጥ ይረከባል፡፡
  • ተጫራቾች የሚታተሙ ህትመቶችን በሆስፒታሉ ናሙና መሰረት አድርገው ማቅረብ አለባቸዉ ፡፡
  • ተጫራቾች ሆስፒታሉ ከአሁን በፊት ምንም አይነት ማስጠንቀቂያ ያልተሰጣቸው መሆን አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች ሆስፒታሉ ካቀረበው ዝርዝር ዋጋ ማቅረቢያ ውጭ በሌላ ዋጋ ማቅረቢያ ማቅረብ አይችሉም፡፡ የጨረታ ሰነዱንም ለሌላ ማስተላለፍ አይቻልም፡፡
  • ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ አይነት ባሸነፉበት ጥራትና ዋጋ ዝርዝር መሰረት ልዩነት ቢኖረዉና የጥራት ችግር ቢከሰት በራሳቸዉ ውጭ እንደገና የመተካት እና የማቅረብ ግዴታ አለባቸዉ፡፡
  • ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ናሙና ሳያቀርቡ ሙሉ ለሙሉ ይዘው ቢመጡና እቃዉ ተፈላጊ አይነት ሳይሆን ቢቀር ሙሉ ለሙሉ ወዲያዉኑ መልሰዉ በራሳቸዉ ወጭ ናሙና አቅርበዉ በማረጋገጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡ተጫራቾች ጨረታ ካሸነፉ በኋላ ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ፣ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ በባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆስፒታሉ ገንዘብ ቤት ድረስ ቀርበው ማስያዝ አለባቸው::
  • ተጫራቾች አሸናፊነታቸዉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀን ዉስጥ የዉል ማስከበሪያ የአሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ በውልና ማስረጃ ውል በመፈፀም ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  • ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛዉ ቀን 4፡0ዐ ድረስ የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ማስገባት ይችላሉ ፡፡የጨረታ ሳጥኑ ወዲያዉኑ ይታሸጋል በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት ይከፈታል፡፡ በአላት ቀን ከሆነ በቀጣይ ስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል ::
  • የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ60ቀን ፀንቶ ይቆያል፡፡
  • ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ ፋ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት፣ በስልከ ቁጥር 0116813390 ወይም በፋክስ 0116811008 ቁጥር በመላክ መጠየቅ ይቻላል፡፡
  • መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን በሙሉ የመሠረዝ መብቱ እንዲሁም ግዥዉን በጥቅል ወይም በተናጠል አወዳድሮ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

ደብረብርሃን አጠቃለይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

Save Tender