በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምዕራብ ቅ ጽ/ቤት የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ የቀላል የመኪና ጌጣጌጥ፣ የመኪና ታፒሴሪ፣ የመኪና ባትሪ እና ሻተር መጋረጃ፣ አቅጣጫ ጠቋሚ እና እራይ፣ ተልኮ የማስታወቂያ የጽሕፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃ፣ የአይሲቲ እቃዎች ፣ እስካነር /Scanner/ GPS፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ምዕራብ/ቅ/ጽ/ቤት/05/ 2018
በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምዕራብ ቅ ጽ/ቤት የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ የቀላል የመኪና ጌጣጌጥ፣ የመኪና ታፒሴሪ፣ የመኪና ባትሪ እና ሻተር መጋረጃ፣ አቅጣጫ ጠቋሚ እና እራይ፣ ተልኮ የማስታወቂያ የጽሕፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃ፣ የአይሲቲ እቃዎች ፣ እስካነር /Scanner/ GPS፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች የዕቃ ግዥና አገልግሎት ግዥ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፤
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN Number) ማቅረብ የሚችሉ፣
- የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ለሚኒባስ ሰርቪስ ብቻ ሊብሬና የሶስተኛ ወገን ሰነዶችን ማቅረብ የሚችሉ፣
- ለጨረታ ማስከበሪያ ብር ለእያንዳንዱ 5,000 (አምስት ሺህ ብር) አዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምዕራብ ቅ/ጽ/ቤት ስም የዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታው ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 150 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበትቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት አቃቂ ቃሊቲ ውሀ ልማት 5000 ተገጣጣሚ ቤቶች ግቢ ውስጥ በቅርንጫፉ ጽ/ቤት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የቴክኒክና ፋይናንሻል ሰነዶች ተለያይቶ በተለያየ ፖስታ ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ፋይናንሻል ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ኦሪጂናል እና ቴክኒካል ኮፒ ተብሎ በአራት ፖስታ በማድረግ ኮፒ እና ኦርጅናሉ በጉልህ ተጽፎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ማስታወቂያ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ ከ2:00-11:00 ድረስ የጽ/ቤቱ ቢሮ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጅው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተከታታይ 10 /የስራ ቀናት/ ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ2፡00 - 11:00 ቅዳሜ ከ2፡00-6:00 መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከሰዓት 4፡30 በቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ ሆነው ሲገኙ የአሸነፉባቸውን እቃዎች ወይም አገልግሎት የውል ማስከበሪያ ለማስያዝና ከመስሪያ ቤቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት ለመፈጸም መስማማት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታውን ሙሉ ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፣ አቃቂ ቃሊቲ ውሀ ልማት 5000 ተገጣጣሚ ቤቶች ግቢ ውስጥ
ለበለጠ ማብራሪያ፣ 0931804871, 0911 37 35 12 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምዕራብ ቅ/ጽ/ቤት
