Tender Detail

Tender Details


በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ሥር ለኩ አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለተቋሙ ለህክምናና ለተለያዩ ሥራ ሂደቶች አገልግሎት ላይ የሚውሉ ከታች ከተራ ቁጥር 1-3 የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን ሆስፒታሉ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የለኩ ጠቅላላ ሆስፒታል


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ሥር ለኩ አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለተቋሙ ለህክምናና ለተለያዩ ሥራ ሂደቶች አገልግሎት ላይ የሚውሉ ፡-

1ኛ) ለሆስፒታሉ የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች ፤ መድሃኒቶች የህክምና ላቦራቶሪ ኬሚካሎች እና ሪኤጀንቶችን

2ኛ) አላቂ የፅዳት ዕቃዎች

3ኛ) የቢሮ ፅህፈት መሣሪያዎችን

ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን ሆስፒታሉ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡ በዚሁ መሠረት ተጫራቾች የሚከተለትን ቅድመ ተከተል ሁኔታዎችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ
  2. የዘመኑን ማለትም 2018 የበጀት ዓመቱን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN No/ ያለው።
  4. ጨረታውን አሸንፎ የሚያቀርበውን ዕቃ ንብረት ጥራት ለማረጋገጥ ናሙና ማቅረብ የሚችል፡፡
  5. ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ወይም አቅራቢ ዕቃውን ንብረቱን እስከ ሆስፒታሉ በራሱ ወጪ የሚያቀርብ
  6. አሸናፊ ሆኖ የሚጠራው ግለሰብ አቅራቢ ድርጅት የዕቃውን የንብረቱን ጥራት እና ደረጃ በጨረታ ሰነድ ላይ ሆስፒታሉ ባስቀመጠው መልኩ ውል ገብቶ በውሉ መሠረት የሚያቀርብ፡፡
  7. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ለተከታታይ ዘወትር የስራ ሰዓት እና ቀናት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከሆስፒታሉ ግፋን ዳይሬከረቶሬት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ወይም በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ በግልፅ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታውን እንዲያስገቡና በተገለፀው ቀን ከሆስፒታሉ ግፋን ዳይሬክቶሬት ለጨረታው በተዘጋጀ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዘርፍ ለእያንዳንዱ ጨረታ ማስከበሪያ 10,000 /አስር ሺህ / ብር ሲፒኦ (CPO) በመስሪያ ቤቱ ስም ለለኩ ሆስፒታል ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  10. ጨረታው የሚገባበት ቀን ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ የሥራ ቀናት ተቆጥሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ ለየዘርፉ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እዲያስገቡ ሆኖ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡
  11. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶችን ያላሟሉ ተጫራቾች ከውድድር ውጪ ይሆናሉ፡፡

 

ማሳሰቢያ ፡- ጨረታው የሚገባበት ቀን መደበኛ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀንና ሰዓት ይሆናል። ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 046-226-0373 ደውሎ መረዳት ይችላል፡፡

 

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ ሥር ለኩ አጠቃላይ ሆስፒታል

 

Save Tender