Tender Detail

Tender Details


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአረጋውያን መጠለያና መጦሪያ የሰንሻይን ፊላንትሮፊ ፋውንዴሽን ማዕከል የሚከተሉትን ዕቃዎች ማለትም የአረጋውያን አልባሳትና የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ የንፅህና መጠበቂያና የፅዳት ግብዓቶች፣ የግንባታና ህንጻ መሳሪያዎች፣ የምግብ ግብዓቶች፣ የኪችን ዕቃዎች፣ የፅህፈትና ቢሮ ዕቃዎች፣ የህትመት ስራዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአረጋውያን መጠለያና መጦሪያ የሰንሻይን ፊላንትሮፊ ፋውንዴሽን ማዕከል


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአረጋውያን መጠለያና መጦሪያ የሰንሻይን ፊላንትሮፊ ፋውንዴሽን ማዕከል የሚከተሉትን ዕቃዎች ማለትም የአረጋውያን አልባሳትና የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ የንፅህና መጠበቂያና የፅዳት ግብዓቶች፣ የግንባታና ህንጻ መሳሪያዎች፣ የምግብ ግብዓቶች፣ የኪችን ዕቃዎች፣ የፅህፈትና ቢሮ ዕቃዎች፣ የህትመት ስራዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

በጨረታው ለመወዳደር የተቀመጡ መስፈርቶች፡-

  1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው የዘመኑ ግብር የተከፈለበት እና የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እና የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከድርጅቱ ግዢ ከፍል መውሰድ ይኖርባቸዋል፤
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የእቃ ዝርዝርና ቫትን ያካተተ ዋጋ ተሞልቶ እና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማህተምና ፊርማ በማኖር በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ፖስታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ በግዥ ክፍል ውስጥ ባለው በታሸገ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
  5. በመክፈቻ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ያለመገኘት የጨረታውን ሳጥን መክፈቻ ሥነ ስርዓት አያስቀርም።
  6. የጨረታው ሳጥን በአስረኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በድርጅቱ ግዢ ክፍል ይከፈታል፣
  7. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ድርጅቱ ናሙና ራሱ አቅረቦ ለዕጩ ተወዳደሪዎች ለእይታ አስቀርቦ በናሙና መሰረት እንዲያቀርቡ የሚያደርጋቸው ግዥዎች መኖራቸውን እንዲታወቅ፤ የሚቀርቡ ናሙናዎች የሚቀርቡበት ጊዜ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ሲሆን የሚቀርቡበት ለናሙና ማስቀመጫ በተዘጋጀው ከፍል ነው። ተጫራቾች ያቀረቡት ናሙና በሚመረመርበት ወቅት በእቃው ባህሪ ምክንያት ቢበላሽ ቢጠፋ ካሳ አይከፍልም። ውጤት ከገለጸበት አንስቶ በ6 ወር ውስጥ ካልወሰዱ በውርስ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።
  8. አሸናፊ ተጫራች ውል ተዋውሎ ያሸነፈባቸውን ግብአቶች ማዕከሉ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳና የግብአቶች መጠን ማቅረብ ይኖርበታል፤
  9. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. መደበኛ የጨረታ ሰነድ (SBD) ከተቋሙ የተወሰዱትን አንብቦ እና የተሟላ አድርጎ ሙሉ በሙሉ የጨረታ ሰነዱን መመለስ (ማስገባት) ይኖርበታል።

 

አድራሻ

ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ጀርባ

ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር 011-668 90 70 / 09 94 71 20 45 በዚህ ስልክ ቁጥር ደውለው፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአረጋውያን መጠለያና መጦሪያ የሰንሻይን ፊላንትሮፊ ፋውንዴሽን ማዕከል

 

Save Tender