ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት Computer ብዛት 9 (ዘጠኝ) Printer ብዛት 7 (ሰባት)፣ Laptop ብዛት 7 (ሰባት) እና Scanner ብዛት 1 (አንድ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Berhanena selam printing enterprise (ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 004/18
ድርጅታችን Computer ብዛት 9 (ዘጠኝ) Printer ብዛት 7 (ሰባት)፣ Laptop ብዛት 7 (ሰባት) እና Scanner ብዛት 1 (አንድ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲስ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 300.00 ከፍለው በመግዛት ፋይናንሽያል የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000 በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
ጨረታው 2/4/ 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በየእለቱ ቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ) ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት
ስልክ ቁጥር 011-1-55-52-30
ድረ ገፅ (www.ethbspe.org)
Berhanena selam printing enterprise
አዲስ አበባ
