Tender Detail

Tender Details


የደ/ብርሃን ደም ባንክ አገልግሎት ለ2018 በጀት አመት ሎት 1 የጽ/መሣሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የተሸከርካሪ ኢንሹራንስ ዋስትና ፣ ሎት 4 የቀላል ተሽከርካሪ ቅባትና ዘይት ፣ ሎት 5 ህትመት ፣ ሎት 6 ኤሌከትሮኒክስ ፣ ሎት 7 የግብርና እቃዎች እና ሎት 8 ቋሚ ዕቃዎች አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የደ/ብርሃን ደም ባንክ አገልግሎት


የጨረታ ቁፕር 001/2018

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የደ/ብርሃን ደም ባንክ አገልግሎት ለ2018 በጀት አመት ሎት 1 የጽ/መሣሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የተሸከርካሪ ኢንሹራንስ ዋስትና ፣ ሎት 4 የቀላል ተሽከርካሪ ቅባትና ዘይት ፣ ሎት 5 ህትመት ፣ ሎት 6 ኤሌከትሮኒክስ ፣ ሎት 7 የግብርና እቃዎች እና ሎት 8 ቋሚ ዕቃዎች አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው ፣

3. የግዥ መጠኑ 200000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከደም ባንኩ ገንዘብ ቤት ቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይችላሉ፣

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር 2000/ሁለት ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.አ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፣

6. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሃሣቡን አርጂናሉን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ሥ/ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣

7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ን/አ/ደ/ስ/ሂደት 3 በቢሮ ቁጥር ጨረታው በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው ቀን 4፡01 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ4፡3ዐ ሰዓት ይከፈታል ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የሥራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፣

8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

9. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በአካል በመገኘት በመላከ ወይም በስልክ ቁጥር 011-637-56-71/0912334091/በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

ማሳሰቢያ:- መ/ቤቱ በሚቀርበው የእቃ ጥራት ላይ አይደራደርም፡፡ እንዲሁም መ/ቤቱ ባቀረበው ሳንፕል መሠረት ማቅረብ አለበት፡፡ ኢንሹራንስ ዋስትናን በተመለከተ በደ/ብርሃን ከተማ የአገልግሎት ሰጪ ቅርንጫፎች መኖር አለበት፡፡

የደ/ብርሀን ደም ባንክ አገልግሎት

Save Tender