Tender Detail

Tender Details

  • Company የሐረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን
  • Address ሐረር ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 025-666-7531
  • Website
  • Deadline20 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price800.00
  • Bid Security30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር)
  • opening date2025-11-20 00:00:00
  • Categories Insurance Service

የሐረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በተመደበ መደበኛ በጀት የራሱ ንብረት የሆኑትን የከባድ እና የቀላል እንዲሁም የሞተር ሳይክል ተሽከርካሪዎች የሶስተኛ ወገን እና ሙሉ የተሽከርካሪ ኢንሹራንስ ሽፋን ለሁለት አመት አወዳድሮ ለመስጠት ይፈልጋል፡፡

የሐረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የግዥ መለያ ቁጥር ፡ - ሐ /ክ/ው/ፍ /ባ/መኪ/ኢ ን ሹ- 01/2018

የግዥ ርእስ ፡ 1 “ኢንሹራንስ ሸፋን ግዥ ለመፈፀም

 

ተራ ቁጥር

የተሽከርካሪው አይነት

የተሸከርካሪው መለያ

የተሽከርካሪ ብዛት

1

የከባድ መኪና እና ማሽነሪ

ከባድና ማሽነሪ

7

2

የቀላል መኪና

ቀላል

20

3

የሞተር ሳይክል

የሞተር ሳይክል

27

 

 

 

ድምር 54

 

  1. የሐረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በተመደበ መደበኛ በጀት የራሱ ንብረት የሆኑትን የከባድ እና የቀላል እንዲሁም የሞተር ሳይክል ተሽከርካሪዎች የሶስተኛ ወገን እና ሙሉ የተሽከርካሪ ኢንሹራንስ ሽፋን ለሁለት አመት አወዳድሮ ለመስጠት ይፈልጋል፡፡ የኢንሹራንስ ሽፋን ለመስጠት በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ የኢንሹራንስ ኩባንያዎችን በሙሉ መወዳደር ይችላሉ።
  2. ጨረታውን መወዳደር የሚፈልግ በኢንሹራንስ ኩባንያ ዘርፍ የተሰማሩ ህጋዊ የሆነ ድርጅት የሚከተሉትን ክራይቴሪያዎች ማሟላት ግዴታ ነው።
  • በዘርፉ የታደሰ 2017 ዓ.ም የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል።
  • በኢንሹራንስ ዘርፍ ተመዝግቦ የተሰማራ መሆን ይኖርበታል፡፡
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ማቅረብ የሚችል።
  • የዘመኑን ግብር ለመከፈሉ ከሚመለከተው አካል ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።
  • ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ
  1. ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንት ከታች ከተራ ቁጥር 11 በታች በተጠቀሰው አድራሻ እየቀረቡ የጨረታ ዝርዝር ሰነዱን የማይመለስ ብር 800.00 (ስምንት መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ።
  2. ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀናት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ይሆናል።
  3. ጨረታው የሚከፈተው በመጨረሻ በ15ኛው ቀን ሲሆን 15ኛው ቀን የሥራ ቀናት ካልሆነ በቀጣይ ሥራ ቀናት ላይ የሚከፈት ይሆናል። በመክፈቻ ስራ ቀናት እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ጨረታውን ማስገባት የሚቻል ሲሆን በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 የጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
  4. ጨረታው ከማስገቢያው ሰዓት ዘግይቶ የመጣ ተጫራች ተቀባይነት የለውም።
  5. በጨረታው አከፋፈት ወቅት ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአካል ተገኝተው መከታተል ይችላሉ።
  6. ጨረታው በአየር ላይ ፀንቶ የሚቆይበት 45 ቀናት ይሆናል።
  7. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) CPO ወይም ቅድመ ሁኔታ የማይጠይቅ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል።
  8. ለበለጠ ማብራሪያ ከታች በቀረበው ስልክ ቁጥር ደውለው ማብራሪያ መጠየቅ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
  9. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ የሐረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

ስልክ ቁጥር 025-666-7531 ወይም 025-666-75-32 ፖስታ ሳጥን ቁጥር 198 ፋክስ 025-666-65-18

 

የሐረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

 

Save Tender