በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት አንድ የጽህፈት መሳሪያዎች /ስቴሽነሪ/ ግዥ ለመፈጸም እና ሎት ሁለት የመጓጓዣ/ትራንስፖርት/ በግልጽ ጨረታ በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ እቃዎቹን መግዛት እና አገልግሎቶቹን ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት አንድ የጽህፈት መሳሪያዎች /ስቴሽነሪ/ ግዥ ለመፈጸም እና ሎት ሁለት የመጓጓዣ/ትራንስፖርት/ በግልጽ ጨረታ በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ እቃዎቹን መግዛት እና አገልግሎቶቹን ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።
- ለሎት ሁለት የመኪናውን ለብሬ ማስያዝ የሚችል፡፡
- ለሎት አንድ ግዢ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ ከ1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎች እና አገልግሎቶች ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጽ/ቤቱ በመሂ/1 ማስያዝ የሚችል እና አሸናፊ ከሆነ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋው 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጽ/ቤቱ በመሂ/1 ማስያዝ የሚችል፡፡
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ውል የሚወስደው በበየዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን እና ፍትህ ጽ/ቤት ይሆናል፡፡ አሸናፊ የሚለየው በጠቅላላ ድምር መሆኑን የተረዳ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከ 24/02/2018 ዓ/ም እስከ 08/03/2018 ዓ/ም የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ በመክፈል በበየዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ሰአት እሁድ ቅዳሜን ጨምሮ እስከ 11፡30 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በ09/03/2018 ዓ/ም 4:00 ታሽጎ ከቀኑ 4፡30 ህጋዊ ተጫራቾች /ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት እና የሚታሸግበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ካላደር ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን 4፡00 ታሽጎ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ህጋዊ ተጫራቾች /ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሣጥኑ ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ እቃዏቹንም ሆነ አገልግሎቶቹን ድል-ይብዛ ከተማ ስድስቱም ንብረት ክፍሎች ድረስ ማቅረብና ማጓጓዝ የሚችልና የጫኝ አውራጅን ወጪ በራሱ መሸፈን የሚችል እና ሎት ሁለትን እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ/ም ድረስ ውል ወስዶ ማቅረብ የሚችል እና በተጠየቀ በአምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ አገልግሎቶቹን ማጓጓዝ የሚችል።
- በመ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚመታው ማህተም ከንግድ ፍቃዱ ጋር ቀጥተኛ /ተዛማጅ የሆነ መሆን አለበት። በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በተጫራቾች መመሪያ ወይም በስልክ ቁጥር 0975643488 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት
