በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግሥት ትምህርት ቢሮ ቦንጋ የትምህርት ኮሌጅ በ2018 የበጀት ዓመት ለኮሌጁ ትምህት ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Bonga College of Education (ቦንጋ የትምህርት ኮሌጅ)
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግሥት ትምህርት ቢሮ ቦንጋ የትምህርት ኮሌጅ በ2018 የበጀት ዓመት ለኮሌጁ ትምህት ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ፡-
- ሎት-1 የተለያዩ ኮምፒውተሮች፣ ላፕቶፖች፣ ፕሪንተሮች ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ የኔትዎርክ ዕቃዎችና መለዋወጫዎች፣ የሴኩሪቲ ካሜራ፣ የኮምፒውተር መለዋወጫዎች፣
- ሎት-2. የመኪና ጎማ፣
- ሎት 3. የመኪና ጥገና ጨረታ፤
- ሎት-4 የመኪና ዕቃ መለዋወጫዎች ጨረታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፣
- በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው፣
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው
- ሌሎች በተጫራች መመሪያ መ/ቤቱ የሚጠይቃቸውን መረጃዎች የሚያሟሉ ድርጅቶች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በመ/ቤቱ የተዘጋጀውን ዝርዝር የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ከኮሌጁ ግዥ ንብረት አስ/ ዳይሬከቶሬት ክፍል በመውሰድና የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር በመክፈል ዋጋ በመሙላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት የኢትዮጵያ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ሲረጋገጥ የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) 10% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ 16 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ቦንጋ የትምህርት ኮሌጅ ግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ጨረታ ክፍል ይከፈታል፤ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በጨረታ ሳጥን አከፋፈት ወቅት /ሥነ-ስርዓት ላይ ተጫራቾች አለመቅረብ የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉልም፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ያሸነፏቸውን ዕቃዎች እስከ ቦንጋ የትምህርት ኮሌጅ ድረስ አቅርቦ ማስረከብ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ ለዕጩ ተጫራቾች በጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ ላይ የገለጻቸውን የጨረታ ስነ-ስርዓቶች፣ መስፈርቶችና ሌሎች መረጃዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከገለጻቸው የሚለዩ ከሆነ በጨረታ ሰነዱ ላይ የገለጻቸው የበላይነት ይኖረዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሲገዙ የተጫራች መመሪያ አብሮ መያያዙን ማረጋገጥ እና መመሪያውን መከተል ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ማንኛውም የመጫረቻ ሰነድ ጨረታው በወጣበት ቋንቋ መሆን ይገባዋል።
- ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
ቦንጋ የትምህርት ኮሌጅ
