Tender Detail

Tender Details


በአቃቂ ክ/ከተማ በወረዳ 9 ስር የሚገኘው ቂሊንጦ ቁ.2 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ አቃዎችን በየሎቱ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአ/ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ትምህርት ጽ/ቤት ቂሊንጦ ቁ.2 ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዢ መለያ ቁጥር 001/2018

 

በአቃቂ ክ/ከተማ በወረዳ 9 ስር የሚገኘው ቂሊንጦ ቁ.2 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ አቃዎችን በየሎቱ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ለየሎቱ ሲፒኦ በማስያዝ ማቅረብ የምትችሉ ተጫራቾች ከዚህ በታች ያሉትን እያንዳንዱ መረጃ መስፈርቶች/ በጥንቃቄ ትኩረት ሰጥታችሁ በማንበብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

           ለሎት 1. የደንብ ልብስ - 30,000.00 ብር                                   ለሎት 4. አላቂ የፅዳት እቃ - 35,000.00 ብር

           ለሎት 2. አላቂ የቢሮ ዕቃ - 20,000.00 ብር                               ለሎት 5. ልዩ ልዩ መሣሪያ - 5,000.00 ብር

           ለሎት 3. አላቂ የትምህርት ዕቃ - 20,000.00 ብር                      ለሎት 6. የሕክምና እቃዎች - 5,000.00 ብር

  1. በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ እና ቲን ነምበር /TIN NO/ ያላቸው።
  2. የዘመኑ ግብር የከፈሉና በአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. በተጨማሪ አሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ከባንክ በተረጋገጠ /ሲ.ፒ.አ/ ከላይ በተጠቀሱት የሎት አይነቶች መሠረት ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።
  5. የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ የማይመለስ 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁ.3 መግዛት ይችላሉ።
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በፖስታ በማሸግ ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. ጨረታው የሚዘጋው በጋዜጣ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በሥራ ቀናት ውስጥ በ4፡00 ሰዓት ይሆናል። እንዲሁም ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ ዕለት 4፡30 ይሆናል።
  9. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈውን ዕቃ በሚደረገው የውል ስምምነት መሠረት በራሱ ትራንስፖርት ቂሊንጦ ቁ.2 የመጀ/ደ/ት/ቤት ማረሚያ ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  10. ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ሰነድ ስትመልሱ ከእያንዳንዱ አላቂና ቋሚ እቃዎችን በመለየት ናሙና /ሳምፕል/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪ፡- መምጣት የማይችሉ ከባድ እቃዎችን በፎቶ ከነስፔስፊኪሽኑ እንድታቀርቡልን እናሳስባለን።
  11. ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል።
  12. የጨረታ አሸናፊ ሆነው ከተገኙ በኋላ 10% /አስር /ፐርሰንት ባሸነፉበት ዕቃ መሠረት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  13. መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋጋ ዝርዝር ስትሞሉ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ እና በፍሉድ የጠፋና የተነካካ የዋጋ ዝርዝር እንዳይኖር እናሳስባለን።
  15. ተጫራቾች በምታቀርቡት ናሙና /ሳምፕል/ ላይ ምንም አይነት የድርጅት ማህተም፧ ስልከ ቁጥር እና ሌሎች ምልክቶች እንዳይኖር ከወዲሁ እናሳስባለን።
  16. ለጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች በሀገር ውስጥ ምርት ብቻ መወዳደር ይችላሉ። ነገር ግን የሀገር ውስጥ ምርት ካልሆነ እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ መግዛት እና ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።ስለሆነም የዋስትና ደብዳቤ የማንቀበል መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።
  17. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 09-20198347/0913-641182 ብለው ይደውሉ።

 

አድራሻ፡- ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ፊት ለፊት ያለው ት/ቤት

 

በአ/ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ትምህርት ጽ/ቤት ቂሊንጦ ቁ.2 ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት

 

Save Tender