ሰበታ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት ለሥልጠና አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Sebeta Polytechnic College (የሰበታ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ሰበታ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት ለሥልጠና አገልግሎት የሚውሉ
- የኮንስትራክሸን ዕቃዎች
- የኤሌክትሪክ እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ለአውቶሞቲቭ ሥልጠና የሚውሉ ዕቃዎች
- የብረታብረት ሥልጠና የሚያገለግሉ ዕቃዎች
- ለልብስ ስፌት እና ቴክስታይል ማሠልጠኛ ዕቃዎች
- ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማሠልጠኛ ዕቃዎች እና
- የተለያዩ የቢሮ (የፈርኒቸር/Furniture) እቃዎች
- የዶሮ መኖ (የእንቁላል እና የቄብ ዶሮ)
- የወተት ከብት መኖ
- ለሥልጠና የሚያስፈልጉ የተለያዩ ዕቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘውን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የታደሰ እንዲሁም የሚፈለግባቸውን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው በቂ ማስረጃ (Clearance) ማቅረብ የሚችሉ፣ አቅራቢዎች ዕቃውን ለማቅረብ የተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ከኮሌጁ ፋይናንስ ክፍል ዘወትር በሥራ ሰዓት ለአንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰበታ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሂሳብ ቁጥር 1000016069225 በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ በተዘጋጀው ሰነድ ያቀረበውን ዋጋ (1%) በባንክ በተመሰከረለት CPO በሰበታ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስም አዘጋጅተው ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ የሚሸጡብትን ዋጋ በመጥቀስ በፖስታ በማሸግ በተባለው ቀን ውስጥ ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ ሞልተው የሚያቀርቡትን ዋናና ፎቶ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ስምና አድራሻ በማድረግ በድርጅቱ ማኅተም በማረጋገጥ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል እንዲሁም ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ቫትን (15%) ያካተተ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃዎች መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃዎች ገቢ የሚሆነው አስፈላጊውን ጥራት ማሟላቱ በባለሙያ ሲረጋገጥ ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ ከስቶክ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሁሉም የጨረታ ማስታወቂያ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ቀን 4:30 የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ከላይ የተገለጸው የመክፈቻ ቀን በዓል ወይንም የሰንበት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር-0113383843/0113380022
የሰበታ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
