የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ተቋማት የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች በስክራፕ (በቁርጥራጭ) መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች፣ የሸገር ዳቦ መሸጫ ባሶች፣ የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸው አስፋልት ሬንጅ /Bitumen ፣ 85/100/፣ የአገለገሉ ሊፍት /አሳንሰር/ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች የተፈታቱ የክሬሸር አካላት DCI ብረታ ብረቶች፣ ጀኔረተሮች፣ የተለያዩ ንብረቶች (የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ ከነመዳሪዎች፣ ቸርኬዎች ፍላፖች፣ በርሜሎች ሌሎችም) ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ተቋማት የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች በስክራፕ (በቁርጥራጭ) መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች፣ የሸገር ዳቦ መሸጫ ባሶች፣ የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸው አስፋልት ሬንጅ /Bitumen ፣ 85/100/፣ የአገለገሉ ሊፍት /አሳንሰር/ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች የተፈታቱ የክሬሸር አካላት DCI ብረታ ብረቶች፣ ጀኔረተሮች፣ የተለያዩ ንብረቶች (የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ ከነመዳሪዎች፣ ቸርኬዎች ፍላፖች፣ በርሜሎች ሌሎችም) ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
- ተጫራቾች ከአፍንጮ በር ወደ 6 ኪሎ በሚወስደው መንገድ ፍቅር ፕላዛ ህንፃ ላይ በሚገኘው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመምጣት የተለያዩ ተቋማት የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ በስክራፕ መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች፣ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ DC ብረታ ብረቶች፣ ዝርዝርና ብዛት የያዘ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) እንዲሁም የተለያዩ ያገለገሉ የንብረቶች (የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ ቸርኬዎች፣ ፍላፖች፣ ከነመዳሪዎች ጀኔረተሮች፣ የተፈታቱ የክሬሸር አካላት፣ በርሜሎች፣ የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸው አስፋልት ሬንጅ /Bitumen 85/100/ ሌሎችም) ዝርዝርና ብዛት የያዘ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ተገኝተው መግዛት ይችላሉ።
- አገልግሎት ጊዜአቸው ያለፈባቸው የአስፋልት ሬንጅ /Bitumen 85/100 የሚጫረት ማንኛውም ተጫራች በዘርፋ የታደሰ የመልሶ መጠቀም ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ዳግም ጥቅም ላይ በሚውልበት ጊዜ በሰውና በእንስሳት ጤና በአካባቢ ላይ ጉዳት ሳያደርሱ መልሶ ጥቅም ላይ ማዋላቸውን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የይሁንታ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል የሚደረግ ይሆናል።
- በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር ዋጋ በአሃዝ እንዲሁም በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 402 ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከከሚታሸግበት ሰዓት ድረስ ተጫራቾች ሰነድን ማስገባት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በአሃዝና በፊደል እንዲሁም በነጠላና በጥቅል በሰጡት ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ አገልግሎቱ ከፍተኛውን ዋጋ ወስዶ ያወዳድራል።
- ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በመግለጽ በመጫረቻ ሠነዳቸው ላይ መፈረም አለባቸው።
- ተጫራቾች በአንድ መለያ ቁጥር (መደብ) ስር ያለውን ንብረት ብዛት በሙሉ መጫረት አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሸያጭ የተዘጋጁትን ተሸከርካሪዎች፣ በስክራፕ በቁርጥራጭ መልክ የሚወገዱ ተሸከርካሪዎች፤ የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸው አስፋልት ሬንጅ /Bituman 85/100፣ የአገለገሉ ሊፍት /አሳንሰር/፣ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች DCI ብረታ ብረቶች የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች (የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ቸርኬዎች፣ ባትሪዎች፣ ፍላፖች፣ ከነመዳሪዎች፣ ብረቶች የተፈታቱ የክሬሸር አካላት፣ በርሜሎች፣ ጀኔረተሮችና ሌሎችም) የአንዱን መስሪያ ቤት በጥቅል መጫረት አለባቸው።
- ተጫራቾች ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ድረስ በመሄድ ንብረቱን አይተው መጫረት ወይም ዋጋ መስጠት አለባቸው። ነገር ግን ንብረቱን ሳያዩ ቢጫረቱና ቅሬታ ቢቀርብ ኣገልግሎቱ ሀላፊነቱን አይወስድም።
- ለሚገዙት የተለያዩ ተቋማት ተሽከርካሪዎችና በቁርጥራጭ መልክ የሚወገዱ ተሸከርካሪዎች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 20 በመቶ (20%)፣ እንዲሁም ለተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ያገለገሉ ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 10 በመቶ (10%) እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ሲ.ፒ.ኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
- የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 504 ይከፈታል። ሆኖም የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉልም።
- ተሽከርካሪዎች የነበረባቸው የቦሎ ዕዳ እና የስም ዝውውር ወጪ በአሸናፊ ተጫራቾች ይሸፈናል።
- አንድ ተጫራች አንድ ተሽከርካሪ እና ከአንድ የመ/ቤት ንብረቶች በላይ መግዛት ይችላል። ሆኖም አንድ ተጫራች ለአንድ ተሽከርካሪ፤ ለአንድ መደብ ንብረት የተለያየ ዋጋ በመስጠት መወዳደር አይችልም።
- በመነሻ ዋጋ በታች የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታ ሳጥን ከተዘጋ በኋላ ኮድ ወይም መለያ ቁጥር ሳይጽፍ ተሳስቻለሁ ወይም ሳልጽፍ ቀርቻለሁ የሚሉ ጥያቄዎች ተቀባይነት የላቸውም።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን መከፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለአገልግሎቱ ገቢ ይደረጋል።
- ንብረቱን በ10 የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ ከጨረታው መውጣት ወይም የሰጠውን ዋጋ ማሻሻል ወይም መለወጥ አይችልም።
- የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጡ ማናቸውም ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-557-32-35 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ። አገልግሎቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት
