Tender Detail

Tender Details


በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ህዳሴ ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት አመት መገልገያ የሚውሉ ሎት 2፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት ( የደንብ ልብስ፣ ሎት 3 ህትመት፣ ሎት 5፣ የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 6 ጥገና እቃዎች፣ ሎት 7. ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 4, መድሃኒቶች መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ህዳሴ ጤና ጣቢያ


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ፡ አግጨ/002/ኦኩስፋ-2/2018 ዓ.ም

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ህዳሴ ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት አመት መገልገያ የሚውሉ ሎት 2፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት1, የደንብ ልብስ፣ ሎት 3 ህትመት፣ ሎት 5፣ የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 6 ጥገና እቃዎች፣ ሎት 7. ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 4, መድሃኒቶች መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላችሁ በተሰማሩበት የስራ መስክ የንግድ ፈቃድን፣ የዘመኑን ግብርለመከፈላቸውና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

2. ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ (vat) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሽያጭ በ የለቱ 200.00/ሁለት መቶ ብር ብቻ ነው፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር ብቻ በድርጅቱ ስም ሲፒኦ በማዘጋጀት ማረጋገጫውን ከመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በጥንቃቄ ሞልተው በመፈራረም እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በወረዳ 14 ህዳሴ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 41 ረዳት ፋይናንስ በመገኘት ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

8. የጨረታው ሳጥን የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው (አስራ አንደኛው) የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ጠዋት 4፡30 ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በወረዳ 14 ህዳሴ ጤና ጣቢያ የግ/ ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 46 ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፡፡

9. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

10. የጨረታውን ሰነድ ሊሞሉ ስርዝ ድልዝ ካጋጠመ ተጫራቹ ሰርዞ ጎኑ ላይ ፊርማውን ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡

11. አሸናፊው ድርጅት ማሸናፉ ከተገለፀበት በ7 ቀናት ውስጥ የመደበኛ ውል ሰነድ መፈራረም ይኖርበታል

12. ጤና ጣቢው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: አድራሻ፦ ወረዳ 14 ህዳሴ ጤና ጣቢያ ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ ገደራ ሳሪ አምፖል አካባቢ

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት

የወረዳ 14 ህዳሴ ጤና ጣቢያ

Save Tender