Tender Detail

Tender Details

  • Company በጅማ ዞን የነዲ ጊቤ ወረዳ መንገዶች እና ሎጂስቲክ ጽ/ቤት
  • Address ጅማ ዞን ነዲ ጊቤ ወረዳ ዲምቱ ከተማ : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 68 07 81 09
  • Website
  • Deadline17 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid Securityየጠቅላላ ዋጋ 2%
  • opening date2025-10-17 00:00:00
  • Categories Rent , Construction Machinery , Construction Vehicle

በጅማ ዞን የነዲ ጊቤ ወረዳ መንገዶች እና ሎጅስቲክ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ በ 2018 ዓ.ም ለሚያከናውነው የተለያዩ መንገዶች ግንባታና ጥገና ማሽነሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

በጅማ ዞን የነዲ ጊቤ ወረዳ መንገዶች እና ሎጂስቲክ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በጅማ ዞን የነዲ ጊቤ ወረዳ መንገዶች እና ሎጅስቲክ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ በ 2018 ዓ.ም ለሚያከናውነው የተለያዩ መንገዶች ግንባታና ጥገና ማሽነሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ አመልካቾች በሙሉ የወረዳው መንገዶችና ሎጀስቲክ ጽ/ቤት በሚያወጣው የጨረታ መስፈርት እና ደንብ መሰረት መጥታችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የማሽነሪዎቹ አይነት

1. ዶዘር CAT D8R                                                      4. ሮለር 16 Ton

2. ግሬደር CAT 140H                                                 5. Shower Truck 16m3

3. ኤክስካቫተር CAT 325 DL, CL                                6 ግልባጭ 14 m3

ሲሆኑ አመልካቾች

  1. ህጋዊ የማሽን ማከራየት ፍቃድ ያላቸው
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢና ቲን ቁጥር ያላቸው፡፡
  3. የ 2018 ዓ.ም የመንግስት ግብር የከፈሉና የንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ
  4. የማሽነሪዎቹ ሞዴል 2016 G.C እና ከዚያ በሁዋላ መሆን አለበት፡፡
  5. ተመሳሳይ ማሽነሪዎችን በተመሳሳይ ሰዓት ሁለት የተለያየ ሳይት ላይ ማስገባት የሚችሉ፡፡
  6. የማሽነሪዎቹን ማስጫኛ ወጪ በራሱ መሸፈን የሚችል።
  7. ከዚህ በፊት በሰሩበት የመልካም አፈጻጸም ምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት በወረዳው ገቢዎች ባለስልጣን ቀርበው የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) የጠቅላላ ዋጋን 2% በባንክ በተረጋገጠ CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች የቅድመ ማጣሪያ ቴክኒካል ዶክመንት በጥንቃቄ በመሙላት እና አስፈላጊ ዶክመንቶችን በማያያዝ ኦርጅናል፣ ፎቶ ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ (CPO) ለየብቻ በሰም በማሸግ ተገቢውን መረጃ በፖስታዎቹ ላይ በጉልህ በመጻፍ ሶስቱንም በሌላ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ እና ቴክኒካል ዶክመንት በማለት መጻፍ ይኖርባቸዋል።
  11. የዋጋ ማቅረቢያ (ፋይናንሻል) ዶክመንት ኦርጂናል እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በሰም በማሸግ ተገቢውን መረጃ በፖስታዎቹ ላይ በጉልህ በመጻፍ ሁለቱንም በሌላ ኤንሽሎፕ አንድ ላይ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ፋይናንሻል ዶክመንት በማለት መጻፍ ይኖርበታል። በመጨረሻም ቴክኒካል እና ፋይናሻል ዶክመንት አንድ ላይ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ አስፈላጊውን መረጃ በጉልህና ግልጽ በሆነ ጽሁፍ በመጻፍ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን እስከ ቀኑ 6፡30 ሰዓት ብቻ በወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  12. ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ6፡30 ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት ውስጥ በይፋ ይከፈታል።
  13. ስርዝ ድልዝ ያለባቸውንና በግልጽ የማይነበቡ አሻሚ ፊደሎች ያላቸው ሰነዶች ሙሉ ለሙሉ ተቀባይነት የላቸውም፡፡

ማሳሰቢያ፡- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጮችን ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አድራሻ፡- ጅማ ዞን ነዲ ጊቤ ወረዳ ዲምቱ ከተማ

ለተጨማሪ መረጃ፡- 09 68 07 81 09/ 09 24 43 75 59 አልያም

በወረዳው መንገዶች ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ አስፈላጊውን መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

 

በጅማ ዞን የነዲ ጊቤ ወረዳ መንገዶች እና ሎጂስቲክ ጽ/ቤት

 

Save Tender