የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን መርማሳ፤ አጁሃ፤ ሃሚድ ውሃ እና ሆርማት ድልድዮች እና መዳረሻ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን እና ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
Ethiopian Railway Corporation (የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን መርማሳ፤ አጁሃ፤ ሃሚድ ውሃ እና ሆርማት ድልድዮች እና መዳረሻ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን እና ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።
|
የግዥው መለያ ቁጥር |
የጨረታው አይነት |
የጨረታ ሰነዱ መሸጫ ዋጋ |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና |
|
ERC/BDD/EP/B041/2025 |
የማሽነሪ እና ተሸከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ (መርማሳ፤ አጁሃ፤ ሃሚድ ውሃ እና ሆርማት ድልድዮች እና መዳረሻ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የሚያስፈልጉ ማሽነሪዎች እና ተሽከርካሪዎች (ሎቤድ፤ ሎደር ሚክሰር ትራክ ኤክስካቫተር፤ ውሃ ቦቴ፤ ነዳጅ ቦቴ፤ ገልባጭ መኪና፤ ሚኒባስ እና ሰረቪስ ፒካፕ) |
ብር 500.00 |
ብር 100,000 |
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የጸና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚያቀርቡት ተሽከርካሪዎች በሙሉ የፈረስ ጉልበታቸው፤ የስሪት ዘመናቸውና ሌሎች ከጨረታ ሰነዱ የተገለፁት መስፈርቶች ተሟልተው መቅረብ አለባቸው። የኪሎ ሜትር እና የነዳጅ ቆጣሪው በትክክል የሚሰራ መሆን አለበት።
- ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 (ስልሳ) ቀናት የሚቆይ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብሄራዊ ባንክ እውቅና ከሰጣቸው ባንኮች ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 32 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ 11/1/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 26/1/2018 ዓ.ም (ጨረታው እስከሚዘጋበት) በኮርፖሬሽኑ መ/ቤት በአካል በመገኘት ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ። ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያውን፤ ፋይናንሻልንና ቴክኒካሉን ሰነዱን በጥንቃቄ በታሽገ አንድ ፖስታ በማድረግ የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 26/1/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በ 26/1/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል። እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፈ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በፋክስ ቁጥር +251114702044 በመልክ ወይም በስልክ ቁጥር 0114702058 ወይም 0114702051 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
(አድራሻ- የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አዲስ አበባ (ሴራሊዮን መንገድ /መሿለኪያ)፣
ስልክ- 0114702058/0114702051/0966800400፣ ፋክስ +251114702044
ኢሜል- erailways@erc.gov.et, bethel erc eng procur@erc.gov.et)
