Tender Detail

Tender Details

  • Company በሀድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ሆሳዕና ከተማ ፡ ደቡብ ክልል : ኢትዮጲያ, Phone: 0916838549
  • Website
  • Deadline09 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security100,000.00
  • opening date2025-10-09 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት የትምህርት ቤት ኪራይ አገልግሎት ግዥ በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።

በሀድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት የትምህርት ቤት ኪራይ አገልግሎት ግዥ በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል። ስለሆነም:

1. የትምህርት ቤት ኪራይ ግዥ

. ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚሆን ቦታ ኪራይ

የጨረታ መመሪያ።

ተጫራቾች በዘርፉ የተመዘገቡበት የዘመኑን የይዞታ ግብር ስለመከፈሉ የሚገልፅ ማስረጃ፣ የግብር ከፋይነት ማስረጃ፣ የይዞታ ማረጋገጫ ማስረጃና ማንነትን የሚገልፅ መታወቂያ ካርድ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ የጨረታ ሰነዱን ከሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ሕንፃ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 011 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከጠዋቱ 2:30-11፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ በሆሳዕና ከተማ ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት በመከፈል ባለንብረቱ ወይም ሕጋዊ ወኪል ኦርጅናልና እንድ ፎቶ ኮፒ የሠነድ ማስረጃ በመያዝ መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነዱ የሚሸጠው ይህ ማስታውቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ተጫራቾች በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ይከፈታል።

ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO/100,000/አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና፣ በማይሻር ሌተር ኦፍ ክሬዲት (L/C) የቀረበ ዋስትና፣ በጥሬ ገንዘብ ወይም በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም የከፍያ ትዕዛዝ ማቅረብ ይጠበቅበታል።

ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አንድ ኦርጅናል፣ ሁለት ፎቶ ኮፒ፣ የተፈረመና ቀን ያለበት የጨረታ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ሞልቶ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /CPO/፣ እያንዳንዱን በፖስታ በማሸግ በመጨራሻም በአንድ በሰም በታሸገ እናት ፖስታ ውስጥ አስገብቶ በማሸግ የአጫራች መስሪያ ቤት ስም፤ የቦታ ስም እና የአከራይ ድርጅት ስም በፖስታው ላይ በመጻፍ የአከራይ ድርጅቱን ማህተም በፖስታው ማሳረፍ፣ በፖስታው ላይ ኃላፊነት በተሰጠው አካል በመፈረም በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ህንፃ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 011 ሁለተኛ ፎቅ ላይ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 3፡00 ድረስ ማስገበት ይኖርባቸዋል።

በእጅ የተሞላ ኮፒ ሰነዶችን እንደ ኦርጅናል ማቅረብ ከጨረታ ውድድር ውጪ ያደርጋል። የጨረታ ዋጋ በሰነድ ላይ በተዘጋጀው ቦታ ብቻ መሞላት አለበት።

ሁሉም ተጫራች በጨረታ ሠነዱ እያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ማህተም ማሳረፍና መፈረም አለበት። ይህ

ካልሆነ ከጨረታ ሂደት ውጪ ያደርጋል።

 

ማንኛውም ተጫራች በሚያቀርበው ሰነድ ላይ አንድ ሐሰተኛ እና የተጭበረበረ ሰነድ ቢገኝ ከጨረታ ሂደት

ውጪ ከተደረገ በኋላ በህግ ተጠያቂ ይሆናል።

በጨረታ ሰነድ ይዘት ላይ ቅሬታ ያለበት ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከመከፈቱ 5 ቀን በፊት ቅሬታውን

በጽሑፍ ለመስሪያ ቤቱ ኃላፊ ቢሮ ቁጥር 001 ማቅረብ ይኖርበታል።

ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ይዘት ላይ የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት አይኖርም።

ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የውክልናውን አርጅናል ይዞ ሲቀርቡ ይሆናል።

ጨረታው በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ተጫራች አለመገኘት የጨረታ አከፋፈት ሂደቱን እያስተጓጉልም።

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0916838549/0949020060

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender