የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ጠጠር የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖች እስከነሎደሩ አቅራቢያዎችን ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ ተከራይቶ ማሠራት ይፈልጋል።
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)
ለመጀመሪያ ግዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ መለያ ቁጥር ፡- ሲ/መ/ባ/002/2018
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ጠጠር የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖች እስከነሎደሩ አቅራቢያዎችን ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ ተከራይቶ ማሠራት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የፕሮጀክቱ ስም |
በክልሉ ውስጥ መንገዱ የሚገኝበት ወረዳ |
የመንገዱ ርዝመት በኪ/ሜ |
|
1 |
አባዬ አቶዬ ጉጉማ ሎት 1 |
ማልጋ |
6 |
|
2 |
ጊዳቦ አስፋልት አዶቴ ቃቻ |
አላታ ወንዶ |
2 |
|
3 |
ጣራቱ ቦኮላ |
ጭሪ |
8 |
|
4 |
ግርጃ ዌሌ |
ሆኮ |
8 |
ስለዚህ፡-
- ኮንስትራክሽን መሣሪያዎችና መገልገያዎች የማከራየት ፍቃድ ያላቸው።
- ገልባጭ መኪና እስከነሎደር የስሪት ዘመን እ.አ.አ 2010 እና ከዚያ በላይ የተሽከርካሪ የመጫን አቅም=14m3 የሆነ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገፅ መመዝገብ ወይም በገንዘብ ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የሚያሳይ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ገልባጭ መኪኖች የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ወይም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ (ውልና ማስረጃ) የተረጋገጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ውክልና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አዲስ ስራ ፍቃድ የሚያቀርቡ ተጫራቾች ከአንድ መንገድ ብቻ እንዲሁም የሥራ ልምድ ያላቸው ተጫራቾች ደግሞ ሁለት መንገድ ብቻ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ከሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ውለታ ገብቶ በአፈጻጸም ችግር ምከንያት ማስጠንቀቂያ ተሰቶት ስራውን ያላጠናቀቀና ውሉ የተቋረጠ የገልባጭ መኪና አከራይ ድርጅት የጨረታ ሰነዱን መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር-5 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (unconditional Bid Bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 0.5% ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በተገለጸው መሠረት ይሆናል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ180 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፋይናንሻል አንድ ዋና ወይም አርጅናል እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና አርጅናል/እና ሁለት ኮፒ ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካቶውና በሁሉም ዶክሜት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
- ጨረታ በአየር ላይ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የተጠቀሰው የመክፈቻ ቀን የእረፍት ወይም የህዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- በጨረታው ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ እና ህጎች አለማክበር በመጫረቻ ሰነዶቻቸው በሁሉም ገፆች ላይ ማህተም እና ፊርማ ያለማድረግ እና ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ ያለበት ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዥ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ መ/ቤት አድራሻ ይከፈታል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡- 0462-128-446
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን
