Tender Detail

Tender Details


የቦሌ አዲስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም ከመንግስት በተመደበልን መደበኛ በጀት እና በውስጥ ገቢ ድጎማ በጀት 1ኛ ዙር ጥቅል ግዢ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በለሚኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳር ወረዳ 09 ት/ጽ/ቤት ቦሌ አዲስ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ /ት/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዢ መለያ ቁጥር፡- 001/2017

 

የቦሌ አዲስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም ከመንግስት በተመደበልን መደበኛ በጀት እና በውስጥ ገቢ ድጎማ በጀት 1ኛ ዙር ጥቅል ግዢ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

 

ተ.ቁ

የሎት ቁጥር

የዕቃው ዝርዝር (ዓይነት)

1

ሎት 1

የስፖርት መምህራን የስፖርት ቱታና ጫማ እንዲሁም የሠራተኞች የደንብ ልብስ

2

ሎት 2

አላቂ የቢሮ (የጽህፈት) መሳሪያዎች

3

ሎት 3

አላቂ የህክምና እቃዎች (የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ መስጫን ጨምሮ)

4

ሎት 4

አላቂ የትምህርት ማበልጸጊያ (የማእከል) የቤተ-ሙከራና የስፖርት እቃዎች እንዲሁም የቧንቧና የኤሌክትሪክ መለዋወጫ እቃዎች

5

ሎት 5

አላቂ የጽዳት እቃዎች

6

ሎት 6

ልዩ ልዩ መሳሪያዎች

7

ሎት 7

የጥገና የኤሌክትሪክ እና የቧንቧ እቃዎች

8

ሎት 8

ቋሚ እቃ እና ለህንጻ አገልግሎት የጥገና እቃዎች

 

ስለዚህ ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢያዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና ከድረ-ገጽ ላይ የአቅራቢነት ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸው ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ክሊራንስ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ናሙና በዝርዝር ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO የባንክ ዋስትና እንዲሁም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ከት/ቤቱ የ/ከ/ፋ/ግ/ን/ አስተዳደር መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. በሎት ቁጥር 7 ለተጠቀሱት ስራዎች ተጫራቾች በቦታው ተገኝታችሁ ዝርዝር መረጃ ከት/ቤቱ ፋ/ግ/ን/አስ/ ማግኘት ትችላላችሁ።
  7. ተጫራቾች በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የለባቸውም።
  8. ተጫራቾች ያላቸውን መረጃዎችና ሰነዶች አሟልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ በት/ቤቱ ፋ/ግ/አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታው የሚከፈተው 10ኛው ቀን ከተጠናቀ በኋላ ባለው የስራ ቀን 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  10. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ለሆኑባቸው ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ ብር 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከት/ቤቱ ጋር የግዢ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል።
  11. መ/ቤቱ ለጨረታው ባወጣው ጠቅላላ ዋጋ 20% ከፍ ወይም ዝቅ ብሎ የግዢ ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል።
  12. ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት ሳያሟሉ በጨረታ ለመሳተፍ መሞከር በህግ ያስቀጣል።

ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በአካል ት/ቤቱ ድረስ በመቅረብ ያነጋግሩን።

አድራሻ፡- ሲኤምሲ አልታድ ሚካኤል ከመስጊድ ወረድ ብሎ ፊጋ መብራቱ ጋር ሲደርሱ ወደ ጎሮ በሚወስደው መንገድ ከቦሌ አዲስ የመጀ/ደ/ት/ቤት አጠገብ ይገኛል።

ለበለጠ መረጃ :- 011-6-59-60-90 / 011-6-59-60-61

 

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የቦሌ አዲስ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

 

Save Tender