ጨረታ መለያ ቁጥር 0001/2017 የት/ቤቱ ቲን ቁ. 0073251921 አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ የመ/ደ/ት /ቤት በ2018 በጀት ዓመት ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል፡፡
አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ የመ/ደ/ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 0001/2017 የት/ቤቱ ቲን ቁ. 0073251921
አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ የመ/ደ/ት /ቤት በ2018 በጀት ዓመት ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል፡፡
የጨረታው አላማ
ትምህርት ቤታችን ማለትም አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ የመ/ደ/ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የትምህርት ግብአቶች ለማሟላት እና ምቹ የትምህርት አሰጣጥ ለማጎልበት ውጤታማ ኅብረተሰብ ለመፍጠር እንዲሁም ግልጸኝነትና ጥራቱን የጠበቀ መልካም አገልግሎት ለመስጠት፣ ኪራይ ሰብሳቢነት ለመቀነስ እና ጠንካራ የልማት ሠራዊት ለመፍጠር ነው፡፡
የጨረታው ግብአቶች፡-
አቃ/ቃ/ክ/ከተማ አስተዳደር አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ የመ/ ደ/ ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች ዝርዝር ማለትም፡-
-
የደንብ ልብስ
-
አላቂ የቢሮ እቃዎች
-
አላቂ የትምህርት እቃዎች
-
የፅዳት እቃዎች
-
ልዩ ልዩ እቃዎችና
-
ኤሌክትሮኒክ እና ማሽነሪ ጥገና
-
ቋሚ እቃዎች
ት/ቤቱ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ እነዚህን እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት ተጫራቾች ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶች እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
* የመንግሥት ዕቃ አቅራቢነት ተመዝግቦ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
* ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
*የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ከገቢዎች ማቅረብ የሚችሉ፡፡
*ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
* ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 6 መግዛት ይችላሉ፡፡
*ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ሞልቶ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
*ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 2 % (ሁለት ፐርሰንት) ሲፒኦ (CPO) በማሠራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊው ከታወቀ በኋላ ለተሸናፊው የስያዙትን ወዲያውኑ ይመለሳል ውል ተቀባይ ከአሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ በባንክ አሠርቶ ማቅረብ አለበት፡፡ ጨረታውን ለማዛባት መሞከር ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑና የጨረታ ማስከበሪያውንም እንደሚወረሱ ማወቅ አለባቸው፡፡ ጨረታው በዘኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጠኛው ቀን በ5፡00 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
*መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
* በማንኛውም የመንግሥት ግዥ ላይ እንዳይሳተፉ ያልታገዱ፡፡
*ተጫራቾች የእቃዎች ናሙና ከየአይነቱ ጨረታ ሳይዘጋ በፊት አንድ በአንድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ት/ቤቱ _ በሚያቀርበው ናሙና ይፈጸማል፡፡ የጨረታው ውጤት ከታወቀ በኋላ የቀረቡት ናሙናዎች ለተሸናፊዎች ሲመለሱ የአሸናፊው ተጫራች ናሙናዎች ግን አይመለስም፡፡
* ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሲያቀርብ ዋናውንና ኮፒ ላይ መፈረምና ማህተም ማድረግ አለበት፡፡ *ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ላይ የሚሞሉትን በመሙላት እያንዳንዱ ቅጽ ላይ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ምንም ሳይጨምር ሳይቀንስ መመለስ ይኖርበታል፡፡
* ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
* ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ወይም ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውን እንዲሁም ስልክ ቁጥራቸውን ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
* ዊዝሆልዲግ ታክስ ከአሸናፊ ድርጅት ይቆረጣል፡፡
* የርክክቡ ቦታ በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ እቃው በንብረት ክፍል ካስገባና ጥራቱ ከተረጋገጠ በኋላ ክፍያ ይፈጸማል፡፡
አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ገላን ኮንዶሚንዬም ገላን ከጤና ጣቢያ ወረድ ብሎ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ብለው ይጠይቁ፡፡ ማሳሰቢያ፡- የጨረታ ሰነዱን ስታስገቡ ሙሉን ሰነድ ሳይቆራረጥ ኦርጅናሉ እና ኮፒውን በ2 ፖስታ አሽገው ሊቀርቡ ይገባል፡፡ ማስገቢያ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 6 ይሆናል፡፡
አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ የመ/ደ/ት/ቤት
