Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ሰሜን ሸዋ ዞን : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0111170171
  • Website
  • Deadline16 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/
  • opening date2025-09-16 00:00:00
  • Categories Metals And Metal Working

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች ለሚገኙ የተለያዩ ብረታ ብረቶችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

የብረታ ብረት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች ለሚገኙ የተለያዩ ብረታ ብረቶችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ተጫራች የብረታ ብረቶቹ በሚገኙበት የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች የሚገኙበትን ሁኔታ በመመልከት መጫረት ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ አላማ በተዘጋጃ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ለሚገዙት እቃ የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ባንክ ማረጋገጫ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማሲያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ያሲያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ዋጋ ሙሉ በሙሉ ክፍያ እንደፈጸሙ የሚመለስ ይሆናል ለተሸነፉት ተጫራቾች ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
  4. ተጫራቹ በዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ስም ፊርማና ማህተም በማድረግ በታሸገ ፖስታ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 18 ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የጨረታ ሰነድ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው የነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ሞልተው ኮፒና ኦርጅናል ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው ተጫራቾች በአካል ሆነ ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 18 ይከፈታል። የመክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ላይ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡
  8. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ የውል ስምምነት ከተፈረመበት ቀን በኋላ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ ለሚ/ወ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ሙሉ ክፍያ በመፈጸም ከከፈለበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈውን እቃ ማንሳት አለበት፡፡
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ መረጃ ስ/ቁ፡- 011-1-17-01-71 ወይም 09-13-57-44-40 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender