በአብከመ ሰሜን ሸዋ ዞን የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ላሉ ሴክተር ጽ/ቤቶች የጽሕፈት መሣሪያዎች፥ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የጽዳት እቃ፡ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በሰሜን ሸዋ ዞን የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/2018
በአብከመ ሰሜን ሸዋ ዞን የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ላሉ ሴክተር ጽ/ቤቶች የጽሕፈት መሣሪያዎች፥ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የጽዳት እቃ፡ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
1, በዘርፉ የወጣ ንግድ ፈቃድና በዘመኑ የታደሰ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የምትችሉ
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ፣ ግዥው ከ200,000 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ መሆኑ ሲታመን ተጫራቹ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ የሚችሉ፤
3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎችን በግልጽ የሚታይ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር እያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. የሚዙ ዕቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች በቀረበው ዝርዝር መሰረት ለጽ/መሣሪያና እላቂ የቢሮ እቃ ብር 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ እና ለጽዳት እቃ ብር 1000/አንድ ሺህ ብር ብቻ/ የጨረታ ማስከበሪያ በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በአጣ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ / CPO በማሠራት የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የምትችሉ፡፡
6. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል ከአጣ/ከ/አስ/ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 2:30 እስኪ 11፡30 ሰዓት ከአጣ/ከ/አስ/ ገንዘብ ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ መግዛትና ለዚሁ በተዘጋጀው በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ፡፡
8. ጨረታው ከ6ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተሃኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
9. ጨረታው በ16ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
10. ተጫራቶች በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሞልተው ማቅረብ አይችሉም፡፡
11. መ/ቤቱ ግዥውን በ20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
12. በጨረታ አሸናፈው ተጫራች ለጽ/ቤቱ ባቀረበው የዋጋ ዝርዝር ከጠቅላላ ዋጋ ከነቫቱ 10% የውል ማስከበሪያ በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ በማስያዝ ውል የመፈረም ግዴታ ያለበት መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡
13. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ማሳሰቢያ
- መረጃ መጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0336610688 ወይም 0921037403 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ጨረታውን የምናወዳድረው በሎት ስለሆነ በሎቱ ውስጥ ላሉ ዕቃዎች በሙሉ ዋጋ መሞላት አለበት ተጫራቹ ካልሞላ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- የገዙትን የጨረታ ሰነድ ምንም ሳያስቀሩ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ሳይቀናነስ መመለስ ይኖርባችኋል።
- በዚሁ ጽ/ቤት ቀደም ሲል ለውድድር ተጋብዘው አሸናፊ ሆነው ለማቅረብ ፈቃደኛ ያልሆኑ ነጋዴዎችን በሙሉ የማናሳትፍ መሆኑን ማወቅ ይኖርባችኋል፡፡
በሰሜን ሸዋ ዞን የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
