Tender Detail

Tender Details


በቂርቆስ ክ/ከተማ የዋ/ቅ/አ/መ/ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም የጥገና ሥራዎችና ለአገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ት/ቢሮ በቂርቆስ ክ/ከተማ ት/ፅ/ቤት የዋልያ ቅ/ አ/መ/ደ/ት/ቤት


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በቂርቆስ ክ/ከተማ የዋ/ቅ/አ/መ/ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም የጥገና ሥራዎችና ለአገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  1. የደንብ
  2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
  3. ህትመት
  4. አላቂ የህክምና ዕቃዎች
  5. አላቂ የት/ት ዕቃዎች
  6. አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
  7. ልዩ ልዩ መሳሪዎች መጽሐፍፎች
  8. ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች
  9. ጥገና ዕድሳት ሥራዎች

ከህጋዊ አቅራቢዎች ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እንፈልጋለን መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተለውን መስፈርቶች ሟሟላት አለባቸው

  1. በጨረታው በጥቃቅን አነስተኛ የተደራጀ ሆነው የዕድገት ደረጃቸው አነስተኛ ታዳጊ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ከሚመለከተው ክፍል ደብዳቤ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የሀገር ውስጥ ግብር አጠናቀው የከፈሉ መሆን እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ
  3. Tin ነበር ማቅረብ የሚችል
  4. ቫት ተመዝገቢነት ማቅረብ የሚችል
  5. የንግድ ምዝገባ ማቅረብ የሚችል
  6. የፌዴራል የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
  7. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን የተሰጠ ማቅረብ የሚችል
  8. የአቅረቢነት ዝርዝር ውስጥ ያሉ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  9. ከሁለት አመት ወዲህ ሁለት አመት ያልሞላው የስራ ልምድ ቢያንስ አምስት ቦታ የሰሩበት የተሟላ የስራ ልምድ ኮፒና ኦርጅናል ማቅረብ የሚችል
  10. የጨረታ ማስከበሪያ 20,000 ሃያ ሺ ብር በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም በመስሪያ ቤታችን የውስጥ ገቢ አካውንት ያስገባበትን ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ዋስትና ማስከበሪያ 20,000 ብቻ ለግንባታ ተጫራቾች ብቻ ይመለከታል
  11. ተጫራቾች የአሸነፉበትን የጥገና ሥራ ክፍያ የሚከፈላቸው ሥራውን ሰርተው ሲያጠናቅቁ ነው።
  12. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል በእያንዳንዱ ኮድ የሚመለስ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ 10,000 (አስር ሺ ብር) ማቅረብ ይኖርቦታል፡፡
  13. ለጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ 200 ሁለት መቶ ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በዋልያ የመጀ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 1 (አንድ) በግንባር በማቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  14. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን እቃ ናሙና ጨረታውን ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባችኋል ናሙና ለማይቀረብላቸው ዕቃዎች ፎቶ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  15. የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጅናል በመለየት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በተለየዩ አሽገው ሲያምጡ CPO ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  16. ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የዋጋ ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ከነቫቱ በግልፅ ሞልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 10ኛው የሥራ ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሣጥን ቢሮ ቁጥር 1 ማስገባት ይችላሉ፡፡
  17. ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት 10ኛው ቀን በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  18. የጨረታ አሸናፊ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዕቃ የጠቅላላ ዋጋን 10 ፐርሰንት ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ማስያዝ
  19. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ከቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን ዝቅ ብሎ

ስልክ ቁጥር፡- 011-4-67-27-36

 

በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ት/ቢሮ በቂርቆስ ክ/ከተማ ት/ፅ/ቤት የዋልያ ቅ/ አ/መ/ደ/ት/ቤት

 

Save Tender