Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Rural Roads Construction Agency (የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ)
  • Address ባህርዳር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-222-11-00
  • Website
  • Deadline09 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityየእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1%
  • opening date2025-09-09 00:00:00
  • Categories Petroleum Products Fuel, Diesel , Oil And Lubricant

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል ናፍጣ፣ የተሽከርካሪና ማሽነሪ ዘይትና ቅባት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ በሎት/ በጥቅል አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Amhara Rural Roads Construction Agency (የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ)


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- 03/2018

 

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል ናፍጣ፣ የተሽከርካሪና ማሽነሪ ዘይትና ቅባት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ በሎት/ በጥቅል አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚሀ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ለውድድር ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፤
  3. የተሽከርካሪና ማሽነሪ ዘይትና ቅባት የግዥ መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ በተ/ቁ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ የናፍጣ፣ የተሽከርካሪና ማሽነሪ ዘይትና ቅባት ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመ/ቤቱ አካውንት ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 በመክፈል የባንከ ዲፖዚት ስሊፕ በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ቀን 04/13/2017 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ስም በተከፈተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000012858586 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ፖሊፕ ከፋይናንሻል ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስያዝ አለባቸው። ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 500,000.00 /ከአምስት መቶ ሺህ ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ብቻ ማስገባት ይችላሉ።
  8. ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን ማለትም ዋናና ኮፒ (Original and Copy) በማለት በአንድ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ ኦፈሰር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት/ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ቀን 04/13/2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትና ሌሎች ታክስ እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋን ጨምሮ መሆን አለበት።
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በቀን 04/13/2017 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን በ8፡30 ሰዓት ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል።
  11. የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  12. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058-2-22-11-00 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058-3-22-51-55/ 058-2-22-110 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
  14. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፊርማና ማህተም ማድረግ አለባቸው። በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡

ባህር ዳር

 ፖ.ሣ.ቁ. 382

 

አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ

 

Save Tender