የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለ2018 የበጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ ለሚገነቡ የመንገድ ስራ ፕሮጀክቶች እና ለመንገድ ጥገና ስራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
Amhara Rural Roads Construction Agency (የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ)
የማሽነሪ እና ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ገመኮኤ 04/2018 ዓ/ም
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለ2018 የበጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ ለሚገነቡ የመንገድ ስራ ፕሮጀክቶች እና ለመንገድ ጥገና ስራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የጸና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ የሰርቪስ መኪና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ያልሆኑ መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚቀርቡት ተሽከርካሪዎች በሙሉ የፈረስ ጉልበታቸው፣ የስሪት ዘመናቸውና ሌሎች ከጨረታ ሰነዱ የተገለፁት መስፈርቶች ተሟልተው መቅረብ አለባቸው።
- የኪሎ ሜትር እና የነዳጅ ቆጣሪው በትክክል የሚሰራ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የጠቅላላ ዋጋውን 1% ለማሽነሪ ሆኖ ለሰርቪስ መኪና በቀን፣ ገልባጭ መኪና በሰዓት፣ ለውሃ ቦቴ በሰዓት፣ ለገልባጭ መኪና በሜ/ኩብ እና ሎቤድ በኪሎ ሜትር ብር 10,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 (ስልሳ) ቀናት የሚቆይ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብሄራዊ ባንክ እውቅና ከተሰጣቸው ባንኮች ብቻ ወይም በጥሬ ገንዘብ በኮንስትራሽን ኤጀንሲው ስም በተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000012858586 ግቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኮፒውን ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ23/12/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 03/01/2018 ዓ.ም ዋናው መ/ቤት ባህር ዳር በአካል በመገኘት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሂሳቡን ፋይናንሻልንና ቴክኒካሉን ሰነዳቸውን በአግባቡ በመጠረዝ በፖስታ በማሽግ የተሟላ አድራሻ በመፃፍ በሁለት ፓስታ ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ ተዘጋጅቶ ከግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 03/01/2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ በአካል በመገኘት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮንስትራክሽን ኤጀንሲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ወይም ከግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 03 በ03/01/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል። እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- የዋጋ መሙያ ቅፁ ላይ ስርዝ ድልዝ እና ፍቀት ካለው ፊርማ ያለው ቢሆንም ስርዝ ድልዝ ባለው ቦታ ላይ ከጨረታው ውድድር ውጭ ይደረጋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፈ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በፋክስ ቁጥር 058-222-11-00 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058-320-55-55 ወይም 058-222-11-07 በመደወል ወይም በኤጀንሲው ድረ-ገጽ www.arrca.gov.et ማግኘት ይችላሉ፡፡
ባህር ዳር
ፖ.ሣ.ቁ. 382
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
