የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በ2018 ዓ.ም በታቀደው መሠረት ለከተማ አስተዳደር በሥሩ ለሚተዳደሩ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ከሎት 01/2018 እስከ ሎት 02/2018 ያሉት ዕቃዎችን ግዥ ለመፈጸም በመስኩ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና /ኢኮ/ ልማት መምሪያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በ2018 ዓ.ም በታቀደው መሠረት ለከተማ አስተዳደር በሥሩ ለሚተዳደሩ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ከሎት 01/2018 እስከ ሎት 02/2018 ያሉት ዕቃዎችን ግዥ ለመፈጸም በመስኩ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚገዙ ዕቃዎች፡-
-
- የጽህፈት መሣሪያ ሎት/ምድብ 01/2018
- የጽዳት ዕቃዎች ሎት/ምድብ 02/2018
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡-
- በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒአ (CPO) ወይም ቢድቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (ለአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዥ ኬዝቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ16ተኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 046-220-99-63/046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና /ኢኮ/ል/መም/ያ
ሀዋሳ
