በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ በሎት የተጠቀሱትን ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን ተጫራቾችን በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ህ/ተ/በጎ/ፈ/ማ/ኮ 01/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ በሎት የተጠቀሱትን ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን ተጫራቾችን በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፤
|
ተ.ቁ |
የጨረታ አይነት በሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ |
|
1 |
ሎት 1. የህትመት አገልግሎት |
30,000.00 ብር |
|
2 |
ሎት 2. የኩነትና የመድረክ መሪ አገልግሎት |
30,000.00 ብር |
|
3 |
ሎት 3. የሆቴል አገልግሎት |
30,000.00 ብር |
|
4 |
ሎት 4 ኬተሪንግ አገልግሎት |
20,000.00 ብር |
|
5 |
ሎት 5. የአላቂ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ውሃ አቅርቦት |
15,000.00 ብር |
|
6 |
ሎት 6. የትራንስፖርት/አውቶቢስ፣ የሚኒባስና የጭነት መኪና |
20,000.00 ብር |
|
7 |
ሎት 7. የቋሚ ዕቃዎች ግዥ |
30,000.00 ብር |
|
8 |
ሎት 8. የጋራዥ አገልግሎት ግዥ |
30,000.00 ብር |
|
9 |
ሎት 9. የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና እና ሰርቪስ |
5,000.00 ብር |
|
10 |
ሎት10. የማስታወቂያ የሚዲያ/ አገልግሎት |
20,000.00 ብር |
|
11 |
ሎት11. የክህሎትና የባህሪ/ማይንድ ሴት/ ስልጠና አገልግሎት ግዥ |
10,000.00 ብር |
- ተጫራቾች በጨረታ መሳተፍ የሚችሉት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ንግድ ምዝገባ፣ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት እና የአቅራቢነት ተመዝጋቢ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ለመኪና 3ኛ ወገን ኢንሹራስ፣ የባለቤትነት ደብተር፣ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም ሌሎች ለጨረታ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን አያይዞ በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 /አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ በግዥ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀውን ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ሰነድ በማይመለስ የአንዱን ሰነድ በ200 /ሁለት መቶ ብር/ ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 /አስር/ የስራ ቀናት ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ ማታ 11፡30 ሰዓት ድረስ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ የቴክኒካልና የፋይናንሻል ሰነዶቻቸውን ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በአንድ ፖስታ ከተጓዳኝ ማስረጃዎች ጋር ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው መዝጊያ ሰአት አስቀድሞ በ11ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰአት ድረስ በማስገባት የሚታሸግ ሲሆን ጨረታው በዚሁ ዕለት 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ማግስቱ የበአል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ የአከፋፈት ሂደቱ ከሎት 1 እስከ 6 በ11ኛው ቀን 4፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ከሎት 7 እስከ 11 ያለው ደግሞ በማግስቱ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ሲመልሱ ናሙና ለተጠየቀባቸው የማምጣት/የማቅረብ ግዴታ አለባቸው። እንዲሁም ናሙና ማቅረብ ለማይቻልባቸው ዕቃዎች ገላጭ ፎቶ ተያይዞ እንዲቀርብ እያሳወቅን ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳችሁን ስትመልሱ ተቋማችን ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድና በጨረታው በተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ መሠረት ብቻ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡ ከዚህ ውጪ በራሱ ሰነድ የሚያቀርብ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመሸጫ ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት የፀና ይሆናል፡፡
- ተቋማችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቹ ለጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ሲያሰራ ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት 60 ቀናት በተጨማሪ የ28 ቀናት ተጨምሮበት መቅረብ አለበት፡፡
- አድራሻ፡- ፒያሳ እሪበከንቱ ቢቲ ታወር 3ኛ ፎቅ ይገኛል፡፡ ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር +251111124738
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን
