Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline08 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security100,000.00
  • opening date2025-09-08 00:00:00
  • Categories Petroleum Products Fuel, Diesel , Oil And Lubricant

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የተሽከርካሪ ነዳጅ እና የተለያዩ የመኪና ቅባቶችን ለዋናው መሥሪያ ቤት አገልግሎት የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የረጅም ጊዜ ውል በመግባት አብሮ መስራት ይፈልጋል።

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: SSNT-T562

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የተሽከርካሪ ነዳጅ እና የተለያዩ የመኪና ቅባቶችን ለዋናው መሥሪያ ቤት አገልግሎት የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የረጅም ጊዜ ውል በመግባት አብሮ መስራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡

1. የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የንግድ ምዝገባ ምዝገባ ምስክር ወረቀት/TIN/ ያላቸው እና በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፍቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

2. በነዳጅና አቅራቢነት ህጋዊና የታደሰ ምስክር ወረቀት ያለው፣

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T562 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ የጨረታ ቁጥሩን፣ የድርጅታቸውን ስም እና ስልክ ቁጥር ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላከ የጨረታ ሰነዱን በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንከ ዋስትና (Unconditional Bank Guaran-tee) “በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ” ስም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡

5. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ከፍል እስከ ጳጉሜ 03 ቀን 2017 ዓ.ም 5፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው በተመሳሳይ ቀን በ5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት ይከፈታል፡፡

ስተጨማሪ ማብራሪያ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ፣

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

ስልክ ቁጥር፡ +251-115-17-89-18

ኢ-ሜይል: ESAYASTS@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻስ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

Save Tender