በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ት/ፅ/ቤት የወ/ሮ ቀለመወርቅ ጥሩነህ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የጽህፈት መሳሪያዎች፤ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የትምህርት ዕቃ ግዥ፣ ቋሚ ዕቃ ግዥ፣ የጥገና ዕቃ ግዥ፣ የሕትመት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ቀለመወርቅ ጥሩነህ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
የመጀመሪያ ዙር የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ብ.ግ.ጨ 001/18
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ት/ፅ/ቤት የወ/ሮ ቀለመወርቅ ጥሩነህ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የጽህፈት መሳሪያዎች፤ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የትምህርት ዕቃ ግዥ፣ ቋሚ ዕቃ ግዥ፣ የጥገና ዕቃ ግዥ፣ የሕትመት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱ አቅራቢ ተጫራች የሚከተሉትን ነጥቦች በመገንዘብ የጨረታ ሰነዱን መስሪያ ቤታችን በግንባር በመቅረብ መግዛትና መወዳደር ይችላል፡፡
1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ በመንግስት ግዢ ዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስከር ወረቀትና የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. የጨረታ ሰነዱ በሁለት ፖስታዎች ዋና/orginal/ እና ቅጂ/copy/ ኤንቬሎፕ ታሽጎ በጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታው ማስረከቢያ ሰዓት ከመድረሱ በፊት በወ/ሮ ቀለመወርቅ ጥሩነህ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል መግባት ይኖርበታል፡፡
3. ተጫራቾች ናሙና ለማይቀርብባቸው ዕቃዎች አጭር መግለጫ /specification/ ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. እያንዳንዱ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ /bid bond / በየሎቱ ብር 2,500 /ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር/ በcpo ከዋናው (orginal) የጨረታ ሠነድ ውስጥ አድርጎ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
5. ተወዳዳሪዎች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት መስሪያ ቤታችን በግንባር በመገኘት የማይመለስ 200.00 / ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
6. የጨረታ ሰነዱ ጨረታው አየር ላይ በዋለ በ11ኛው የስራ ቀን በ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
7. የጨረታ ሠነድ መቀበያ ሰዓት ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- አዲስ አበባ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ከፒያሳ ወደ አዲሱ ገበያ መንገድ ሾላ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከፍ ብሎ
ስልክ :- 011-1-26-32-42/011-1-55-45-73
የወ/ሮ ቀለመወርቅ ጥሩነህ ሁስተኛ ደረጃ ት/ቤት
