Tender Detail

Tender Details


በደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የኣሪ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በፑል ለሚተዳደሩ ሴክተር መ/ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት አላቂ የቢሮ ዕቃዎች/ጽሕፈት መሣሪያ/፣ የሕትመት ሥራ፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፣ የታሸገ ውሃ ፣ የተሽከርካሪ መኪና መለዋወጫ፣ ለተሸከርካሪ መጓጓዣ /ሞተር ሳይክል/ግዥ፣ ፕላንት ማሽነሪ /የኤልከትሮኒክስ/ ዕቃዎች ግዥ፣ ለቋሚ የቢሮ ዕቃዎች /ፈርኒቸር/ ግዥ እና የተለያዩ የሕንፃ መሣሪያ ግዥ መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የኣሪ ዞን ፋይናንስ መምሪያ


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የኣሪ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በፑል ለሚተዳደሩ ሴክተር መ/ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት አላቂ የቢሮ ዕቃዎች/ጽሕፈት መሣሪያ/፣ የሕትመት ሥራ፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፣ የታሸገ ውሃ፣ የተሽከርካሪ መኪና መለዋወጫ፣ ለተሸከርካሪ መጓጓዣ /ሞተር ሳይክል/ግዥ፣ ፕላንት ማሽነሪ /የኤሌክትሮኒክስ/ ዕቃዎች ግዥ፣ ለቋሚ የቢሮ ዕቃዎች /ፈርኒቸር/ ግዥ እና የተለያዩ የሕንፃ መሣሪያ ግዥ መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።

  1. በሁሉም መስኮች ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ፍቃድ ያሳደሱ ፡፡
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin number) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሠርተፍኬት (VAT) ማስረጃ ያለው፤
  3. ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የንግድ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው፣ እንዲሁም
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች /ጽሕፈት መሣሪያ/ 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ ፣ የሕትመት ሥራ 10,000 ብር (አስር ሺህ ብር ብቻ) ፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች 10,000 /አስር ሺህ ብር/፣ የታሸገ ውሃ 10,000 /አስር ሺህ ብር/፣ የተሸከርካሪ መኪና መለዋወጫ 10,000 /አስር ሺህ ብር/፣ ለተሸከርካሪ መጓጓዣ /ሞተር ሳይክል/ ግዥ 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/፣ ፕላንት ማሽነሪ /የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ 10,000 ብር (አስር ሺህ ብር ብቻ) ፣ ለቋሚ የቢሮ ዕቃዎች /ፈርኒቸር/ ግዥ 10,000 ብር (አስር ሺህ ብር ብቻ) እና የተለያዩ የሕንፃ መሣሪያ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በሕግ ከታወቀ ባንክ በጥሬ ገንዘብ፤ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፤ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬድት ማቅረብ ይችላሉ፡፡

ከላይ የተገለጹትን ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ከኣሪ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ከግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 12 ቀርቦ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን ሰነድ በ16ኛው /አስራ ስድስተኛው/ የሥራ ቀን ከሆነ ብቻ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡30 ሰነዱን አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።

ጨረታው በዚያው ቀን 8፡30 ሰዓት ባለቤቱ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች ያለመሟላት የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉልም፡፡

ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ኦርጅናል ዶክመንቶቻቸውን ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ- ስልክ ቁጥር 0916135977 ወይም 0926104134

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የኣሪ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

 

Save Tender