በደቡብ ኢትዮጵያ ወላይታ ዞን ጉኑኖ ሐሙስ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለመንግስት ሴክተር መ/ቤቶች የሚያስፈልጉ ዕቃዎች እና አገልግሎት ግዥ በየሎት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን በመጋበዝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጽም ይፈልጋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ወላይታ ዞን ጉኑኖ ሐሙስ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር መደበኛ 1-2018
በደቡብ ኢትዮጵያ ወላይታ ዞን ጉኑኖ ሐሙስ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለመንግስት ሴክተር መ/ቤቶች የሚያስፈልጉ ዕቃዎች እና አገልግሎት ግዥ በየሎት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን በመጋበዝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጽም ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፤
|
ሎት |
የዕቃ አገልግሎት አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO |
የማይመለስ የሰነዱ መግዣ ዋጋ |
|
ሎት-1 |
ጽ/መሣሪያ እና ጽዳት ዕቃ |
10,000 |
200 ብር |
|
ሎት-2 |
የመኪና ጎማ |
10,000 |
200 ብር |
|
ሎት-3 |
የማዳበሪያ ማጓጓዣ መኪና ኪራይ |
3000 |
200 ብር |
|
ሎት-4 |
ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች |
10,000 |
200 ብር |
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ከመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ
- ተጫራቾች የግብር ከፋይ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና የተጨማሪ እሴት /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑ
- የጨረታ አሸናፊ ሲሆኑ የጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ ተደርጎ የውል ማስከበሪያ 20% ለማስያዝ ፍቃደኛ የሆነ።
- የሰነዱን ኦርጅናሉንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) ሙሉ አድራሻቸውንና የድርጅቱን ስም በመጥቀስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ፣ እንዲሁም የማይነበብ ከሆነ ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 1 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋቸውን ሞልተው የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም አድርገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ30 ቀን በኋላ በሚውለው በሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ:- 0913921119 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የጉኑኖ ሐሙስ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
