Tender Detail

Tender Details


የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለወረዳው ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 8 ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2018

 

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለወረዳው ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ሎት1 የደንብ ልብስ፣ ሎት2 የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት3 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ሎት 4 የቢሮ ቋሚ እቃ፣ ሎት 5 የትራንስፖርት (የመኪና ኪራይ)፣ ሎት 6 የህትመት ሥራዎች፣ ሎት 7 የአዳራሽ ዲኮር የድንኳን እና የሞንታርቦ ኪራይ፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው አካተው ማቅረብ ያለባቸው ሰነዶች፡-

  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ያለው፣
  • የወቅቱን የመንግሥት ግብር የከፈሉ፣
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ፣
  • የታደሰ ንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ፣
  • በመንግሥት ጨረታ ለመሳተፍ በአቅራቢነት የተመዘገቡ፣
  • ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ አቅራቢዎች የጨረታውን ሰነድ የሺ ደበሌ በሚገኘው ወረዳ 8 አስተዳደር ፋይናንስና ጽ/ቤት አዲሱ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 12 ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከላይ የተገለጹትን መረጃዎች በማቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  • ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ሎት1 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) ፣ ሎት2 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር)፣ ሎት3 25,000.00 (ሀያ አምስት ሺህ ብር)፣ ሎት4 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር)፣ ሎት5 12,000 (አስራ ሁለት ሺህ ብር)፣ ሎት6 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር)፣ ሎት7 12,000 (አስራ ሁለት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  • የግዢ ውል በሚፈጸምበት ጊዜ መ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተመለከተው የዕቃ ብዛት እስከ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  • ጨረታው ከወጣበት በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡15 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ ቤት ይከፈታል፡፡
  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113839716 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  • መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • መ/ቤቱ የሚገኝበት ልዩ ቦታ መጠሪያው ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር ልዩ ስሙ የሺ ደበሌ

 

በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 8 ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender