የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የአንቲ ቫይረስ ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ/ዕግ/02/11/2017 ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Federal Housing Corporation (የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን)
የጨረታ ማስታወቂያ
ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ/ዕግ/02/11/2017
- የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የአንቲ ቫይረስ ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ/ዕግ/02/11/2017 ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ለኮርፖሬሽኑ አገልግሎት የሚያገለግል የአንቲ ቫይረስ ግዥ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ቴክኒካል ሰነዳቸውንና ዋጋቸውን በተለያዩ በታሸጉ ኤንቨሎፖች ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ ሥርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ መንገሥት በወጣው የመንግሥት የግዥ አዋጅ መሠረት ሲሆን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል።
- የተሟላ የአማርኛ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀር በሚገኘው በተለምዶ የስነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 209 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነደቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 209/212 ለዚሁ ታሸጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ወይም 12/12/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆና ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም ሲፒኦ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 12/12/2017 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተር 2ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
- ኮርፖሬሽኑ በሚያወጣው ፕሮግራም መሠረት አሸናፊው ተጫራቾ የአንቲ ቫይረስ ግዥውን በኮርፖሬሽኑ ቅጥር ግቢ ያስረክባለ።
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 515 7728 ወይም 011 553 9535 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
