Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ እና በስሩ ላሉት ፖሊስ ጣቢዎች በ2018 በጀት ዓመት ሎት 1 ከቦሌ ፖሊስ መምሪያ ከነበረበት ቦታ የተለያዩ የቢሮ እቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት ጭኖ አዲስ ወደ አስገነባው የራሱ ህንፃ እስከ ስድስተኛ ፎቅ ድረስ በመውሰድ በየተዘጋጀላቸው ቢሮዋች የሚያስገባ፣ ሎት 2. የቢሮ መጋረጃ ጨርቅ፣ ሎት 3. የእስረኛ ቀለብ፣ ሎት 4 የመኪና ጎማ ግዥ፣ ሎት 5. የተለያዩ የካሜራ ማን ዕቃዎች፣ ሎት 6. በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚሰራ ሃምሳ ሰው የሚይዝ ደረጃ ሁለት የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ መኪና ኪራይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር BPM 0001/2018 ዓ.ም

 

በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ እና በስሩ ላሉት ፖሊስ ጣቢዎች በ2018 በጀት ዓመት ሎት 1 ከቦሌ ፖሊስ መምሪያ ከነበረበት ቦታ የተለያዩ የቢሮ እቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት ጭኖ አዲስ ወደ አስገነባው የራሱ ህንፃ እስከ ስድስተኛ ፎቅ ድረስ በመውሰድ በየተዘጋጀላቸው ቢሮዋች የሚያስገባ፣ ሎት 2. የቢሮ መጋረጃ ጨርቅ፣ ሎት 3. የእስረኛ ቀለብ፣ ሎት 4 የመኪና ጎማ ግዥ፣ ሎት 5. የተለያዩ የካሜራ ማን ዕቃዎች፣ ሎት 6. በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚሰራ ሃምሳ ሰው የሚይዝ ደረጃ ሁለት የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ መኪና ኪራይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ሲሆን፦ ስለዚህ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውና የታደስ የዘመኑ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ እንዲሁም ከአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ሎት 1 ከቦሌ ፖሊስ መምሪያ ከነበረበት ቦታ የተለያዩ የቢሮ እቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት ጭኖ አዲስ ወደ አስገነባነው የራሱ ህንፃ እስከ ስድስተኛ ፎቅ ድረስ በመውሰድ በየተዘጋጀላቸው ቢሮዎች የሚያስገባ.............

ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/

ሎት 2 የቢሮ መጋረጃ ጨርቅ ..................................................... ብር 20,000.00 /ሀያ ሺህ ብር

ሎት 3. የእስረኛ ቀለብ ..................................................... ብር 50,000.00 /ሀምሳ ሺህ ብር/

ሎት 4. የመኪና ጎማ ግዥ ..................................................... ብር 6,000.00 /ስድስት ሺህ ብር/

ሎት 5. የተለያዩ የካሜራ ማን ዕቃዎች .....................................................ብር 8000.00 /ስምንት ሺህ ብር/

ሎት 6. በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚሰራ ሃምሳ ሰው የሚይዝ ደረጃ ሁለት የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ መኪና ኪራይ ..................................................... ብር 2,000.00 /ሁለት ሺህ ብር/

ተጫራቾች በሎት 2 እና በሎት 3 ናሙና (ሳምፕል/ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው ፡፡ በሎት 1፣ በሎት 4፣ በሎት 5 እና በሎት 6 መስሪያ ቤቱ በሚያቀርበው ሳምፕል ወይም እስፔስፌክሽን መሰረት ሲሆን በዚህ ጨረታ አማራጭ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም ፡፡

  1. ተጫራቾች ታክስን የሚከፍሉበት ክ/ከተማ ፤ የወረዳ ጨረታ መሳተፍ እንዲችሉ የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃዎች በእስፍስኬሽን መሰረት በጥራት ኮሚቴው ወይም በሙያተኛ ተረጋግጦ ገቢ የሚደረግ ይሆናል፡፡
  3. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳቦችን መስሪያ ቤቱ በሰጣቸው የአንድ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ጠቅላላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው መሙላትና የድርጅታችሁን ማህተም ፈርማ ሙሉ ስም (አድራሻቸውን እና ስልክ ቁጥር በመግለፅ አንድ ኦርጅናል እና ኮፒውን በፖስታ ታሽጎ ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ ፡፡ ለመሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፡፡
  5. የጨረታ አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉበትን ንብረት በራሱ የትራንስፖርት ወጪ በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ንብረት ክፍል ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራቾች በፖስታ የታሸጎ ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶችን በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ በ2፡30 ሰዓት እሰከ 11፡30 ሰዓት በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ወረዳ 14 አንበሳ ጋራጅ ጀርባ ቦሌ ከ/ከተማ ገቢዎች አጠገብ ያለው ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 23 የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉ ሲሆን ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚቻለው የጨረታ ሰነድ መሸጥ ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዛው ዕለት 4፡00 ሰዓት ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ 2ተኛ ፎቅ ባዘጋጀው ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የጨረታ መክፈቻ ቀን በስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል ፡፡
  7. የቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፅ/ቤት የተሻለ አማራጮች ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች ቴከኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን /ፋይናሻል/ ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ ማቅረብ አለበት፡፡
  8. አሸናፊ ድርጅቶች የስራ ትዕዛዝ ከተሰጣቸው በ05 ቀን ውል በመፈፀም በተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ ስራውን መጀመር አለበት፣ በተጨማሪም መ/ቤቱ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- 011 - 8 - 27-53 - 61 በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ብላው መደወል ይችላሉ፡፡

 

በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ

Save Tender