Tender Detail

Tender Details

  • Company Kombolcha Customs Branch (የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
  • Address Ethiopia Kombolcha City, Kembolcha, Ethiopia, Phone: 0116730520
  • Website
  • Deadline16 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-16 00:00:00
  • Categories Vehicles Rent , Food Items And Drinks

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት ለ2017/18 በጀት ዓመት ለቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን ሰራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ የህዝብ ማመላለሻ ፣ የደረቅ ጭነት ፣ ክሬን እና የመስክ ተሸከርካሪዎችን ለመከራየት እንዲሁም ባለ ግማሽ ሊትር የማዕድን ውሀ /ለአንድ ዓመት የሚቆይ ውል/ መግዛት ይፈልጋል።

Kombolcha Customs Branch (የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)


 

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ኮ/ቻ/ጉም06/2017

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት

 

  1. ለ2017/18 በጀት ዓመት ለቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን ሰራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ የህዝብ ማመላለሻ ፣ የደረቅ ጭነት ፣ ክሬን እና የመስክ ተሸከርካሪዎችን ለመከራየት እንዲሁም
  2. ባለ ግማሽ ሊትር የማዕድን ውሀ /ለአንድ ዓመት የሚቆይ ውል/ መግዛት ይፈልጋል፤ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የታደሰ ታክስ ክሊራንስ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ብር ለሰራተኞች ሰርቪስ 6,000.00 (ስድስት ሺህ ብር ብቻ) ፤ ለደረቅ ጭነት ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ፤ ለመስክ ተሽከርካሪ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ፤ ለክሬን ኪራይ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ፤ ለባለ ግማሽ ሊትር የማዕድን ውሀ ብር 88,000.00 (ሰማንያ ስምንት ሺህ ብር ብቻ) በባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም Bid Bond (ለ90 ቀናት) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እስከ 08/10/2017 ዓ.ም ደረስ ባሉት ሥራ ቀናት ውስጥ በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሀብት አስተዳደር የስራ ሂደት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. በጨረታው ላይ የሚሳተፉት ህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ደረጃ 01 እና 02 ብቻ ሲሆን ለዚህም ከመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን/ቢሮ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  5. የሚከራዩ የተሸከርካሪ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘነት ይችላሉ
  6. አንድ ተሽከርካሪ ከራሱ ተሽከርካሪ ውጪ የሚያቀርብ ከሆነ ህጋዊ ውክልና እና የባለቤትነት ማስረጃ ሊብሬ ማረጋገጫ ኮፒ ማያያዝ አለበት፤ በውሉ ወቅት ለማመሳከሪያነትም ኦሪጅናል ሊብሬ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሊያስቀርብ ይችላል።
  7. አቅራቢዎች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በጥንቃቄ በመሙላት በእያንዳንዱ ገጽ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በመምታት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በፖስታ ውስጥ አስገብቶ በማሸግ በቅ/ጽ/ቤታችን ስም የጨረታ ቁጥሩንና የግዥውን ዓይነት በመግለጽ በኤንቬሎፕ ላይ በመፃፍ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 09/10/2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የውሃውንና የአገልግሎቱን ዋጋ ሞልተው ከአስፈላጊ ሰነዶች ጋር በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
  9. ጨረታው በ16ኛው ቀን ማለትም ሰኔ 9/10/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  10. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የቀረበውን የጨረታ ሰነድ መቀየር፣ ማሻሻል ወይም ከጨረታው ራስን ማግለል አይቻልም፡፡
  11. የተሰረዘ፣ የተደለዘ፣ የተፋፋቀ ወይም በግልጽ የማይነበብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  12. የጨረታ አሸናፊዎች ዕቃዎቹን እስከ ቅ/ጽ/ቤታችን ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 033 551 1487/ 033 351 1602 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

 

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender