Tender Detail

Tender Details

  • Company Gullele Botanic Garden (ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል)
  • Address ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 በፅዮን ሆቴል 800 ሜትር ገባ ብሎ ልዩ ስሙ አጣሪ ሰፈር ባስው የማዕከሉ ጽ/ቤት ህንፃ ቁጥር 21 ፎቅ ላይ የቢሮ ቁጥር 04 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-54 72 26
  • Website
  • Deadline04 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-04 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Vehicle (Garage Service) , Vehicle Battery , Cloth And Shoes

ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ነገሮች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Gullele Botanic Garden (ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል)


 

የዕቃና አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 03/2017

 

የሎት ዓይነት

ሎት1 የሊፋን አውቶሞቢል ጥገና እና ሰርቪስ አገልግሎት

ሎት2 የሊፋን አውቶሞቢል መለዋወጫ ዕቃዎች

ሎት3 የሠራተኞች ቆዳ ጫማ

ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ባቀረበው ጨረታ ላይ ለመካፈል የዘመኑ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታደሰ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ እና በፌዴራል ግዥ ንብረት አስተዳደር ድረ-ገፅ ላይ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ በዘርፉ የተመዘገቡ መሆኑን የሚገልፅ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

  1. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፤ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተደራጅተው ለሚጫረቱ ተጫሪቾች የጨረታ ማስከበሪያው እና የውል ማስከበሪያው ሲፃፍ በተደራጁበት ዘርፍ መፃፍ አለባቸው፤
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ በየሎቱ የተጠመሩትን የማይመለስ ብር 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ ፤
  3. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ቀደም ሲል ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ፣ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፤
  4. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን ሲያስገቡ በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መሆን ይኖርበታል፡፡ ስሌት ሲሰላ ስህተት ቢኖረው መ/ቤቱ የሚወስደው ነጠላ ዋጋውን ይሆናል፤
  5. ተጫራቾች ለመወዳደር የሚያስገቡት ዋጋ የሚቆይበት ጊዜ 60 ቀን መሆን ይኖርበታል፤ አጭር ጊዜ መስጠት ከውድድር ውጪ ያደርጋል፤
  6. ከላይ የተጠቀሱትን ለጨረታ የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች (ቴክኒካል) ሰነዶች ኦርጂናል ለብቻ በአንድ ፖስታ እና ቴክኒካል ሰነዶች ኮፒ ለብቻ በአንድ ፖስታ በማድረግ በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ፊርማ እና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
  7. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን (ፋይናንሻል) ሰነዶች ኦርጂናል ለብቻ በአንድ ፖስታ እና ፋይናንሻል ሰነዶች ኮፒ ለብቻ በአንድ ፖስታ በማድረግ በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ፊርማ እና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን የጨረታ ሰነዶች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 /አሥራ/ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
  9. የጨረታው አሸናፊ የውል ማስከበሪያ ከአሸነፉት ጠቅላላ ዋጋ 10% /አሥር በመቶ/ (CPO) በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፤
  10. ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመከፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፣
  11. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፤
  12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልከ ቁጥር 0118 96 28 43/0111 54 72 28 ደውለው ያነጋግሩ፡፡

ህንፃ ቁጥር 2 1ኛ ፎቅ ላይ

አድራሻ፡- ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 በፅዮን ሆቴል 800 ሜትር ገባ ብሎ ልዩ ስሙ አጣሪ ሰፈር ባለው የማዕከሉ ጽ/ቤት

 

የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል

 

Save Tender