በደ/ኢ/ክ/መንግስት ትምህርት ቢሮ የአርባ ምንጭ ትም/ኮሌጅ በአርባ ምንጭ ከተማ የተማሪዎች ማደሪያ ግንባታ ሥራን ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
Arba Minch College Of Education (የአርባ ምንጭ ትምህርት ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ኢ/ክ/መንግስት ትምህርት ቢሮ የአርባ ምንጭ ትም/ኮሌጅ በአርባ ምንጭ ከተማ የተማሪዎች ማደሪያ ግንባታ ሥራን ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡-
- ደረጃቸው BC-5/GC-5 እና ከዛ በላይ የሆኑ፣
- ፍቃዳቸውንና የምዝገባ ሠርተፍኬታቸውን ለ2017 ዓ.ም ያሳደሱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡና የታክስ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ዶክመንት የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ቀናት በተቋሙ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና 1,000.000 /አንድ ሚሊዮን ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም ባንክ ዋስትና ከቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንት ኦርጅናል እና ሁለት ሁለት ፎቶ ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ እና ጠቅላላውን በአንድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በ31ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00- 6፡00 ሰዓት ተቋሙ ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ መክተት አለባቸው።
- ጨረታው በ31ኛ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- 31ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- ተቋሙ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ መረጃ ከሰነዱ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እያሣወቅን የደ/ኢ/ክ/መንግስት ባወጣው የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 70/2017 እና በመመሪያው ላይ የተደረገውን ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ሰርኩላር ተፈፃሚ ይደረጋል።
ለበለጠ ማብራሪያ
በስልክ ቁጥር 0468812071
ደ/ኢ/ክ/መንግስት በትምህርት ቢሮ የአርባ ምንጭ ትምህርት ኮሌጅ
አርባ ምንጭ
