Tender Detail

Tender Details

  • Company Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency (የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ)
  • Address ልደታ ክፍለ ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ/የኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ጫፌ አናኒ ህንጻ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-8340-636
  • Website
  • Deadline12 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-12 00:00:00
  • Categories 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles , Generators , Vehicle

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ በቢሮ፣ ዞን፣ ከተማና ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ተሸከርካሪዎች ሞተር ሳይክሎች እና ጀነሬተሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency (የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ)


 

ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 13/2017

 

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ በቢሮ፣ ዞን፣ ከተማና ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ተሸከርካሪዎች ሞተር ሳይክሎች እና ጀነሬተሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 04 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን፤

  1. የኤጀንሲው አድራሻ ፣ አዲስ አበባ ፣ ልደታ ክፍለ ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ /የኢትዮጵያ/ ፈዴራል ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ጫፌ አናኒ ህንጻ ከሚገኘው የኤጀንሲው የግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3rd Floor) ቢሮ ቁጥር-03 በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ከመንግስት ንብረት ዋጋ ግምትና ሽያጭ ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3rd Floor) ቢሮ ቁጥር - 02 መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 - 06፡30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7:30 - 11፡00 ሰዓት ብቻ ነው።
  3. የንብረቶቹን ሁኔታ እስከ ሰኔ 04 ቀን 2017 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2:30- 6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:30 - 11፡00 ሰዓት ድረስ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለፀው ቦታ በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 05/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ድረስ በኤጀንሲው ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው ሰኔ 05 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ5፡00 ተዘግቶ በዕለቱ በ5፡15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ መነሻ ዋጋ 20% /ሃያ ከመቶ/ የጨረታ ማስከበሪያ C.P.O የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በማዘጋጀትና ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

CPO ለማሰራት

የአሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ

Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-1-8340-636

 

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ

 

Save Tender