የሰንዳፋ በኬ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የተለያዩ አይነት ዕቃዎች ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የሰንዳፋ በኬ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፤ የሚገዙ ዕቃዎች
- Lot 1 - አላቂ ዕቃ (Stationary)፤
- Lot 2 - (የጽዳት እቃዎች) Cleaning material
- Lot 3-HDPE fitting & GS fitting
- Lot 4 (ደንብ ልብስ) uniform ናቸው::
ስለዚህ:-
- በተጠቀሱት የንግድ ዘርፎች ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና የ2017 ዓ.ም ግብር የከፈሉ፡፡
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው::
- የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በሰንዳፋ በኬ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 4 በመምጣት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማሰከበሪያ (bid bond) 1% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሠነዱን በመግዛት ዋጋ ሞልቶው በታሸገ ኤንቨሎፕ በሰንዳፋ በኬ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 4 ለዚህ በተዘጋጃው ሳጥን ውስጥ ማስገበት የሚችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን በ7:30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀናት ቅዳሜና ዕሁድ/ በዓላት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-6-86-00-68 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሰንዳፋ በኬ ከተማ ውሃና ፍሳሽ
አገልግሎት ድርጅት
