Tender Detail

Tender Details


የጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአቅራቢዎች ለመግዛት ይፈልጋል።

Tis Isat Water Works PLC (የጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአቅራቢዎች ለመግዛት ይፈልጋል።

 

ተ.ቁ

ሎት

የእቃው አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ

የማቅረቢያ ጊዜ

1

ሎት 1

ስቲል ኬዚንግ (steel casing) አቅርቦት

100,000.00

ከስቶክ

2

ሎት 2

ኤሌክትሮ ሜካኒካል እቃዎች አቅርቦት

50,000.00

45 ቀናት

3

ሎት 3

Flor standing digital signage

30,000.00

45 ቀናት

 

ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ አቅራቢ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከድርጅታችን ድረ-ገጽ www.tisisat.com ማግኘት ይችላል።

የተጫራቾች መመሪያ

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የTIN ሰርተፍኬት፤ በዘርፉ ለመሰማራት የተሰጣቸውን ፈቃድ እና ተያያዥነት ያላቸውን የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  2. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ቴዲ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከድርጅታችን ድረ-ገጽ www.tisisat.com ማግኘት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሰንጠረዥ የተመለከተውን ገንዘብ በCPO ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን እና ቴክኒካል ሰነዳቸውን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለእያንዳንዱን እቃ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል ሞልተው በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው::
  6. ይህ ጨረታ በኩባንያችን የግዥ መመሪያ PR-02/2013 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  7. ኩባንያው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 25% ቢጨምር ወይም ቢቀንስ የጨረታ አሸናፊው ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
  9. የማቅረቢያ ጊዜ ከላይ በሰንጠረዥ በተገለጸው መሰረት መሆን አለበት፡፡ የአቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ ለ90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡
  10. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ማሳሰቢያ፤ ውድድሩ የሚካሄደው እንደ ኩባንያው ፍላጎች በሎት ወይንም በእያንዳንዷ እቃ ነጠላ ዋጋ በሚሞሉት ዋጋ መሰረት ይሆናል፡፡
  • ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥራችን 058-220-48-26 /0583202548/ በፋክስ ቁጥራችን 0582204830 ይጠቀሙ፡፡

 

የጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር

 

Save Tender

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀር፣ ATS እና የሊፍት ዕቃዎች ግዥ

READ MORE
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ያገለገሉ ትራንስፎርመሮች (ስክራፕ) የሐራጅ ሽያጭ

READ MORE
በወረጃርሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የመንገድ መብራት (Street Light Smart Pole) ግንባታ ጨረታ

READ MORE
ድርጅታችን ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የፓወር ፋክተር ኮሬክተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስገጠም ይፈልጋል::

READ MORE