Tender Detail

Tender Details

  • Company ZEMEN CONSTRUCTION CORPORATION (ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን)
  • Address ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 (ባህር ዳርዩኒቨርሲቲ ጥበብ ህንጻ አካባቢ የቀድሞው የአማራ ከተሞች ልማት አ.ማ ግቢ ውስጥ) እና አዲስ አበባ ለገሀር አመልድ ኢትዮጵያ ህንጻ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-218-0538
  • Websitehttps:// zcc.org.et
  • Deadline01 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-01 00:00:00
  • Categories Electrical And Electromechanical , Mechanical Work and Materials

ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እየገነባው ላለው ለምስራቅ ጎጃም ከፍ/ፍር/ቤት ፣ ለምዕ/ጎጃም አስተዳደር ዘርፍ እና ለምዕ ጎጃም ኢኮኖሚ ዘርፍ ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ ሊፍቶች /አሳንሰሮች/ አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ግዥ ለመፈጸም ህጋዊና ብቃት ያላቸው ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ZEMEN CONSTRUCTION CORPORATION (ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን)


 

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 19/2017

 

ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እየገነባው ላለው ለምስራቅ ጎጃም ከፍ/ፍር/ቤት ፣ ለምዕ/ጎጃም አስተዳደር ዘርፍ እና ለምዕ ጎጃም ኢኮኖሚ ዘርፍ ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ ሊፍቶች /አሳንሰሮች/ አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ግዥ ለመፈጸም ህጋዊና ብቃት ያላቸው ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤

  1. በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው/ያላት፤ ጨረታ ለመሳተፍ የታክስ ክሊራንስ ያለው/ያላት፤
  2. የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፣
  3. የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 እና አ/አበባ ለገሃር አመልድ ህንፃ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ 7ኛ ፎቅ ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል እና ፋይናንሻያል ሰነዶች ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) ድረስ ብቻ ባህር ዳር ዋናው ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡ የተጠቀሱት የመክፈቻ እና የመዝጊያ ቀናቶች የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በእለቱ ቀን 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡
  5. ከዚህ በፊት ሊፍቶች /አሳንሰሮች/ አቅርቦት እና ገጠማ ስራ በብቃት እና በጥራት ለመስራታቸው የሚያረጋግጥ የመልካም ስራ አፈፃፀም ማያያዝ ግዴታ መሆኑን መታወቅ አለበት።
  6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር

ባህር ዳር- 058-218-0538/09-13-27-60-57/09-18-71-66-16

አዲስ አበባ ፡- ስልከ ቁጥር 0111265338/0930352410/0967994210

 

የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን

 

Save Tender

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ያገለገሉ ትራንስፎርመሮች (ስክራፕ) የሐራጅ ሽያጭ

READ MORE
በወረጃርሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የመንገድ መብራት (Street Light Smart Pole) ግንባታ ጨረታ

READ MORE
ድርጅታችን ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የፓወር ፋክተር ኮሬክተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስገጠም ይፈልጋል::

READ MORE
Development Bank of Ethiopia extends the deadline for Rack-Mountable 2KVA UPS (Lot-1), IBM TS-4300 T...

READ MORE