የሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው ሥር በተዋቀሩ አምስት ክላስተሮች (ሰበታ ክላስተር፤ ቡራዩ ክላስታር፤ ሱሉልታ ክላስተር፤ ጣፎ ክላስተር እና ገላን ክላስተር) ውስጥ የተለያዩ የግንባታ ማሽነሪዎች ጥገና አገልግሎት ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ማግኘት ይፈልጋል
የሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው ሥር በተዋቀሩ አምስት ክላስተሮች (ሰበታ ክላስተር፤ ቡራዩ ክላስታር፤ ሱሉልታ ክላስተር፤ ጣፎ ክላስተር እና ገላን ክላስተር) ውስጥ የተለያዩ የግንባታ ማሽነሪዎች ጥገና አገልግሎት ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ማግኘት ስለሚፈልግ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን የተወዳደሪዎች መመሪያ በመከተል ይህንን ጨረታ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።
በዚሁ መሠረት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ከሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ ቤት በከፈተው ሲንቄ ሂሳብ ባንክ ቁጥር 1064540111215 ገቢ በማድረግ ዲፖሲት ሲልፑን /Deposit slip ሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ህንፃ 1ኛ ፎቅ ሸገር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት በማቅረብ እና ገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ የጨረታ ሰነዱን 2ተኛ ፎቅ ሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፤ ንብረት አስተዳደር አወጋገድ እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር ክፍል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የተጫራቾቾ ግዴታዎች
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው እንዲሁም በፌዴራል ገንዘብ ሚኒስቴር ወይም ኦሮሚያ ገንዘብ ቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የተጫራች ድርጅት ጋራዡ የንብረት ኢንሹራንስ ያለው እና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ/ ብር በባንክ በተመሰከረ CPO (ሲፒኦ) ብቻ በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ለብቻ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርበታል።
- አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ውል ሲፈርሙ የውል ማስከበሪያ (ዋስትና 10%) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ ብቻ በመሙላት በኦርጅናል እና በኮፒ በመለየት በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው የመንግስት የሥራ ቀናት ሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ህንጻ 2ኛ ፎቅ ግዥ ንብረት አወጋገድ እና አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል። ዕለቱ የመንግሥት ሥራ ቀን ካልሆነ ወይም ቅዳሜ፤ እሁድ እና በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 011-470-9300 በመደወል መረዳት ይችላሉ። አድራሻ: ሳሪስ በአስትሜት ሞተርስ ገባ ብሎ የቀድሞ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ቅጥር ግቢ ውስጥ
የሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
