ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Lihiket Design & Supervision Corporation Bahir Dar (የልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ባህርዳር)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ሠነድ ቁጥር-ልዲቁኮ-06/2017
ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- የቅየሳ መሳሪያዎች አክሰሰሪ
- የላብራቶሪ የስራ ክፍል ልዩ ልዩ አክሰሰሪዎች እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- የጽህፈት መሳሪያ
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት በማሟላት በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የዘመኑን የግብር ግዴታ ስለመወጣታቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ባህር ዳር የግዥ የስራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 29 በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀን ድረስ መግዛት ይቻላል::
- ጨረታው የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ለመገኘት የቻሉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን፤ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በሲፒ ኦ ወይም እንደተጠየቀ ወዲያውኑ በሚከፈል የባንክ ጋራንቲ በፖስታ አሽገው እስከ ጨረታ መዝጊያው ቀንና ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 29 ማቅረብ ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 058-218-02-73 ሞባይል 09-96-14-20-56
በመደወል ወይም
በፋክስ ቁጥር 058-218-05-50 በመላክ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን
ባህርዳር ‐ ኢትዮጵያ
