Tender Detail

Tender Details

  • Company የአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት (Amhara Building Works Construction Company)
  • Address , Phone: 0583217806
  • Website
  • Deadline07 Jan 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Electrical And Electromechanical

የአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ተንቀሳቃሽ የኤሌክትሪክ ዊንች ብቃት ካላቸው ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት (Amhara Building Works Construction Company)


የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር - አህስኮድ  ማሽግ 06/2017

 

የአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ተንቀሳቃሽ የኤሌክትሪክ ዊንች ብቃት ካላቸው ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤

  1. በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው/ያላት
  2. የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም /unconditional bank guarantee/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፤
  3. የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ አማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቀበሌ 11 እና አ/አበባ ለገሀር አመልድ ኢትዮጵያ ህንጻ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል ኦሪጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናት በመቁጠር) ድረስ ብቻ በአህስኮድ የማሽ/ተሽ/መ/ግዥና አቅ/ ኬዝ ቲም ቢሮ (ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበብ ህንጻ አካባቢ የቀድሞው የአማራ ከተሞች ልማት አ.ማ ግቢ ውስጥ) በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው በ15ኛው ቀን በተራ ቁጥር 4 በተገለጸው ቦታ በ8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡ የመዝጊያና መከፈቻ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በዚያኑ ቀን 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡
  6. ዝርዝር የጨረታ መመሪያውን እና የውል ይዘቱን እንዲሁም የሚገዙትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች፣ ዝርዝር በሙሉ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለፀ ስለሆነ ማንኛውም ተጫራች በጥንቃቄ በማንበብ ዋጋቸውን በጨረታ መመሪያው መሰረት መሙላት አለበት፡፡
  7. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::

ስልክ ቁጥር :- 058-3205185/0918164393/0918784490

ፋክስ ፡- 058-218-0538/058-320-4001

 

የአማራ  ህንፃ  ሥራዎች  ኮንስትራክሽን  ድርጅት

Save Tender

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ያገለገሉ ትራንስፎርመሮች (ስክራፕ) የሐራጅ ሽያጭ

READ MORE
በወረጃርሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የመንገድ መብራት (Street Light Smart Pole) ግንባታ ጨረታ

READ MORE
ድርጅታችን ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የፓወር ፋክተር ኮሬክተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስገጠም ይፈልጋል::

READ MORE
Development Bank of Ethiopia extends the deadline for Rack-Mountable 2KVA UPS (Lot-1), IBM TS-4300 T...

READ MORE