Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address በጉራጌ ዞን ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0967441304
  • Website
  • Deadline13 Jan 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Construction

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በCO WASH ፕሮጀክት ምእራብ 4 የገንዘብ ድጋፍ በወረዳው አስማንድር ቀበሌ ከ1-8ኛ ደረጃ ት/ት/ቤት ውስጥ ባለ ሶስት ብሎክ ሁለቱ አራት መቀመጫ ያላቸውና አንድ ብሎክ ሁለት መቀመጫ ያለው የመጸዳጃ ክፍል ለማስገንባት ተጫራቾችን አወዳድሮ ማስራት ይፈልጋል፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  መለያ  ቁጥር  ጌ/ወ/ፋ/ግ/ጨ/ቁ/05/2017

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በCO WASH ፕሮጀክት ምእራብ 4 የገንዘብ ድጋፍ በወረዳው አስማንድር ቀበሌ ከ1-8ኛ ደረጃ ት/ት/ቤት ውስጥ ባለ ሶስት ብሎክ ሁለቱ አራት መቀመጫ ያላቸውና አንድ ብሎክ ሁለት መቀመጫ ያለው የመጸዳጃ ክፍል ለማስገንባት ተጫራቾችን አወዳድሮ ማስራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት በሙሉ የምታሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን፤

  1. የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ አቅራቢዎች፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር በጣት አሻራ ላይ የተመሰረተ እና የተረጋገጠ መረጃ ማቅረብ አለባቸው::
  2. የቫት ተመዝጋቢ የሆናችሁ፡፡
  3. ተጫራቾች በግንባታ ስራ ተቋራጭ በደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑና የዘመኑ ግብር የመክፈል ግዴታቸው የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የተሰጠ ማስረጃና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በግንባታ ስራ በአቅራቢነት የተመዘገቡ እና ስለመመዝገባቸው የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ውክልና ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የብቃት ማረጋገጫ የታደሰ የበጀት ዓመቱ ማቅረብ የምትችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  7. የ2017 በጀት ዓመት ከግብር ነጻ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ (Tax Clearance for 2017 EC)::
  8. ጨረታውን ለማዛበት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑ ለወደፊትም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ በግልጽ ጽሁፍ የተጠየቀውን መረጃ ብቻ በአግባቡ የሚያቀርቡ እና ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን አለበት፡፡ ስርዝ ቢፈጠር በተፈጠረው ቦታ ፊርማ የማኖር ግደታ መሆኑን መረዳት ይጠበቃል።
  10. ተጫራቾች የጨረታው ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሲያቀርቡ፡-

ሀ. ለቴከኒካል ዶክመንት አንድ አርጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒዎች እያንዳንዳቸው በጥንቃቄ በታሸገ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሸግ ቴክኒካል በሚል በመለየት በድርጅቱ ባለስልጣን ተፈርሞበት እና ማህተም የተደረገበት መሆን አለበት፡፡

ለ. ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ አርጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒዎች እያንዳንዳቸው በጥንቃቄ በታሸገ በድርድቱ ባለስልጣን የተፈረመበት እና ማህተም የተደረገበት ሆኖ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሸግ (ፋይናንሻል በሚል በመለየት አስከ 21ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ጌታ ወረዳ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር  ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

  1. ተጫራቾች የግንባታ ስራው የሚሰራበት ቦታ በአካል በማየት ስለማየታቸው ከት/ት ቤቱ የተወከለ አካል የተፈረመበት እና የት/ት ቤቱ ማህተም የተደረገበት መረጃ በመቀበል በቴክኒካል ሰነዱ መጨመር ግዴታ ይሆናል፡፡ ይህንን የቦታ ምልከታ ያላያያዘ ተጫራች ከጨረታው ውጪ ያደርጋል፡፡
  2. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይንም በጨረታ እራስን ማግለል አይቻልም፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 13,000 (አስራ ሶስት ሺህ ብር) በባንከ በተረጋገጠ CPO (በካሽ) ወይም ከመድን ድርጅቶች የሚቀርብ ዋስትና በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረት ለ90 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ቦንድ በጌታ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከኦርጅናል ቴክኒካል ዶክመንት ጋር በማድረግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሸግ ቴክኒካል በሚል በመለየት በድርጅቱ ባለስልጣን ተፈርሞበት እና ማህተም የተደረገበት መሆን አለበት፡፡
  4. ግዥ ፈፃሚ አካል አሸናፊ ከተለየ በኋላ በሚገዛቸው የግንባታ ስራዎች 20% ፐርሰንት የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ጥያቄ ለግዥ ፈጻሚ አካል ማቅረብ የሚችሉት ጨረታው ከመክፈቻ 5 ቀናት በፊት በጽሁፍ መሆን አለበት፡፡
  6. በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በግንባታ የስራ ዝርዝር የያዘ ሰነድ ጨረታው ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በተከታታይ እስከ 21ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ድረሰ የጌታ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት ማይመለስ ብር 200 ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መወሰድ ይቻላል፡፡
  7. የጨረታ ሳጥኑ 21ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ ፣እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 8፡00 ሰዓት በጨረታው ኮሚቴ ታሽጎ በዛው እለት 8:30 ተጫራቶች/ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል /ባይገኙም ይከፈታል።

ማሳሰቢያ ፡-

  1. ግዢ ፈጻሚው አካል ጨረታው በሙሉም (በከፊል) የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
  2. ከዚህ በፊት በአፈጻጸም ምክንያት በወረዳው ውል ገብተው ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ስራው ያላጠናቀቁ ተቋራጮች በጨረታ መወዳደር አይችሉም፡፡
  3. የጨረታው ሂደት ተሻሽሎ የወጣው የክልሉ ግዢ መመሪያ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን እንገልጻለን።
  4. ማንኛውም ተጫራች ለቴክኒካል ዶክመንት የተጠየቀውን መረጃ ብቻ ግልጽ እና በማያሻማ መልኩ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡- 0967441304/0943260350/0961178110/0925838193 መደወል ይችላሉ፡፡

 

በማዕከላዊ  ኢትዮጵያ  ክልል  በጉራጌ  ዞን  የጌታ  ወረዳ  ፋይናንስ  ጽ/ቤት

Save Tender