በደቡብ ኢት/ክ/መንግስት በአሪ ዞን ሰሜን አሪ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት 1ኛ ለጤና ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል በዋን ዋሽ ፕሮግራም አማካይነት በጎዛ ቀበሌ ጤና ጣቢያ ሻወር ቤትና ልብስ ማጠቢያ እና በውርክሽ ቀበሌ ጤና ጣቢያ ሻወር ቤት፤ ልብስ ማጠቢያ እና መድኃኒት ማቃጠያ ግንባታ ሥራ 2ኛ ለትምህርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል በመሎራሻ ቀበሌ ትም/ቤት የመፀዳጃ ቤት እና የውሃ (ቦኖ) ግንባታ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በአሪ ዞን ሰሜን አሪ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢት/ክ/መንግስት በአሪ ዞን ሰሜን አሪ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት 1ኛ ለጤና ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል በዋን ዋሽ ፕሮግራም አማካይነት በጎዛ ቀበሌ ጤና ጣቢያ ሻወር ቤትና ልብስ ማጠቢያ እና በውርክሽ ቀበሌ ጤና ጣቢያ ሻወር ቤት፤ ልብስ ማጠቢያ እና መድኃኒት ማቃጠያ ግንባታ ሥራ 2ኛ ለትምህርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል በመሎራሻ ቀበሌ ትም/ቤት የመፀዳጃ ቤት እና የውሃ (ቦኖ) ግንባታ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ላይ መወዳደር የሚፈልግ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው
- በዘርፋ ንግድ ፍቃድ ያለው
- የዘመኑን ግብር የከፈለ ወይም የንግድ ፈቃድ ያሳደሰ
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ
- የግብር ከፋዮች ምዝገባ ቁጥር /TIN NO/ ሰርተፍኬት ወረቀት ያለው፡፡
- ከጠቅላላ ክፍያ 2% ለመንግስት ግብር መክፈል የሚችል ህጋዊ የሆነ በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ።
- የዚህ ጨረታ ሣጥን የተዘጋጀው አ/አ/ወ/ፋይናንስ/ጽ/ቤት ግቢ ስለሆነ ተጫራቾች የጨረታ ቴክኒካልና ፋይናሻል ኦርጅናል ዶክመንት እና ቴክኒካል ሁለት ኮፒና ፋይናሻል ሁለት ኮፒ በእናት ፖስታ ውስጥ በማድረግ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ መክተት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች CPO 10,000 /አስር ሽህ ብር/ ማስያዝና ቢሮ ቁጥር 7 በመቅረብ 400 ብር በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- በተጨማሪም ተጫራቾች በጨረታ ሠነድ ውስጥ ያሉትን መመሪያዎችን መፈፀም ግዴታ አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል፡፡ ጨረታው የሚቆየው ጊዜ ከ11/4/2017 ዓ.ም እስከ 2/5/2017 ዓ.ም ሲሆን የሚያበቃው በ2/5/2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ላይ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ2/5/2017 ዓ.ም በ4፡10 ሰዓት ላይ ነው::
ማሳሰቢያ፣ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
መረጃ ካስፈለገ በ0977730906 ደወል ይቻላል፡፡
በ ደ /ኢትዮጵያ ሕ/ክ/መ/በአሪ ዞን ሰ/አሪ ወ/ ፋይናንስ /ጽ/ቤት
